ኢትዮጵያዲፕሎማሲ

ባለፉት አራት ዓመታት ከግማሽ ሚሊዮን ዜጎች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እንዳደረገ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 02/03/2018፡- በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የነበሩ ከ17 ሺህ በላይ ዜጎች ከመስከረም ወር ጀምሮ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውም ሚኒስቴሩ አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ትላንት ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ከውጭ ግንኙነት ቁልፍ ሥራዎች አንዱ የዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ መሆኑን ገልጾ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፖሊሲውን በአግባቡ ለመተግበር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በዚህም በሳዑዲ አረቢያ በተለያዩ እስር ቤቶችና ማቆያ ማዕከላት የሚገኙ ከ17 ሺህ በላይ ዜጎች ከመስከረም 05 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሀገራቸው መመለስ መቻሉን ጠቁሟል።

በተመሳሳይ በየመን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 36 ዜጎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን መግለጫው አክልዋል፡፡

በተጨማሪም በማይናመር፣ ላኦስ እና ካምቦዲያ እንዲሁም በሌሎች ሀገራት በተመሳሳይ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚኖሩ ዜጎችን የመመለስ ጥረቱ እንደቀጠለ ነው ብሏል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው ባለፉት አራት ዓመታት በተለያዩ የመካከለኛ ምሥራቅ፣ የአፍሪካ እና እንደ ማይናማር ያሉ የእስያ ሀገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates