ፖለቲካ

የጂቡቲ ገዢ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ጌሌን ለስድስተኛ ጊዜ በእጩነት አቀረበ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 02/03/2018፡- የጂቡቲ ገዢ ፓርቲ ህዳር 8 ቀን 2025 ባወጣው የፕሬስ መግለጫ መሠረት፣ የጂቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌን በሚያዝያ 2026 ለሚደረገው አገራዊ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እጩ አድርገው በይፋ መርጠዋል።

ይህ ማስታወቂያ የተነገረው ከመላው አገሪቱ የተውጣጡ ደጋፊዎች በተገኙበት በፓሌይስ ዱ ፔፕል በተካሄደው ያልተለመደ የፓርቲ ኮንግረስ ወቅት ነው።

ፕሬዚዳንት ጌሌ ሹመቱን በምስጋና ተቀብለው በዓለም አቀፍ ፈተናዎች መካከል ለአንድነት፣ ለመረጋጋት እና ለልማት ያላቸውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

ህዳር 3 ቀን 2025 የጂቡቲ ፓርላማ የፕሬዚዳንቶችን የዕድሜ ገደብ እንዳስወገደ መዘገባችን አይዘነጋም፡፡ ይህም መሪው ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ለስድስተኛ ጊዜ እንዲወዳደሩ መንገድ ከፍቷል።

የጅቡቲ ሕገ መንግስት አንድ ሰው ከ75 ዓመት በላይ ፕሬዝዳንት ሆኖ ማገልገል እንደማችል ይደነግግ ነበር፡፡ የአገሪቱ ምክር ቤት አባላት ይህን ሕገ መንግስት በማሻሻል ነው የ77 ዓመቱ ጊሌን በሚቀጥለው ምርጫ እንዲወዳደሩ ዕድል የፈጠረላቸው፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates