መካከለኛ ምስራቅ
ቱርክ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚኒ ኔታኔያሁ ላይ የእስር ማዘዣ ማውጣቷ ተሰማ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 01/03/2018፡- ቱርክ የእስር ወረቀቱን ያወጣችው በጋዛ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተሳትፈዋል ባለቻቸው 37 የእስራኤል ባለስልጣናት ላይ ነው።
ከ37ቱ መካከል ከቤኒያሚን ኔታኔያሁ በተጨማሪ የመከላከያ ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝ፣ የደህንነት ሚኒስትሩ ኢታማር ቤን ጊቪር እና የጦር አዛዡ ጀነራል ኢያል ዛሚር ይገኙበታል።
ዘ ጋርድያን እንደዘገበው ቱርኪዬ ባለስልጣናቱ በጋዛ አቅደው የዘር ማጥፋት ወንጀልና ሰብዓዊነት ላይ የተቃጡ ጥፋቶችን ፈፅመዋል ስትል ከሳለች።
የአለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች ፍርድ ቤትም ከዚህ በፊት በቤኒያሚን ኔታኔያሁ እና በቀድሞው የመከላከያ ሚኒስትር ዮሃቭ ጋላንት ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቶ የሮም ስምምነትን የፈረሙ ሃገራት ሁለቱ ባለስልጣናት ሃገራቸው ከገቡ አስረው እንዲያስረክቡት መጠየቁ ይታወሳል።



