የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ለአምስት ቀናት የሥራ ጉብኝት ወደ ግብፅ አቀኑ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 20/02/2018፡- የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳይያስ አፈወርቂ ወደ ግብፅ ያቀኑት ፕሬዝደንት አብደል ፋታህ አል ሲሲ ባቀረቡላቸው ግብዣ መሠረት መሆኑን የኤርትራው ራ ማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገ/መስቀል ፅፏል።
ጉብኝቱ በቀይ ባህርና በአፍሪካ ቀንድ ቀጠና ባለው ተለዋዋጭ ሁኔታ ውስጥ በአሥመራና ካይሮ መካከል ባለው ግንኙነት ሌላኛው ምዕራፍ ነው ተብሏል።
የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረመስቀል ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ግንኙነትን በማጠናከር እንዲሁም በአከባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉ አመልክተዋል።
እንዲሁም ፕሬዝደንት ኢሳይያስና ልዑካቸው ጥቅምት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በሚመረቀው የግብፅ ታላቁ ሙዚየም ስነ ስርዓት እንደሚገኙም ሚኒስትሩ ገልጿል። የኤርትራ ልዑክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህን እንደሚያጠቃልል የተገለፀ ሲሆን
ጉብኝቱ በሁለቱ አገራት መካከል በዚህ ዓመት የተደረጉ ተከታታይ የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን ቀጣይ ነው ተብሏሏል።
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ካይሮ መሄዳቸው የተነገረው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማክሰኞ ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በፓርላማ ፊት ቀርበው ኢትዮጵያ ቀጥተኛ የባህር በር እንደሌላት በማንሳት ከተናገሩ ከሁለት ቀናት በኋላ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸውም፤ ኢትዮጵያ ወደብ አልባ የሆነችበትን ታሪካዊ ሁኔታ በመጠየቅ፣ “ሕዝቡም ሆነ የሚኒስትሮች ምክር ቤት፣ እንዲሁም ፓርላማው ኢትዮጵያ የባህር በር መዳረሻን እንድታጣ ሕጋዊም ሆነ ሰነድ አልተገኘም” ብለዋል።



