ኢትዮጵያ

ሶስት ወራት ውስጥ 13,443 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን ኢንሳ አስታወቀ;;

ኢትዮ ሞኒተር፡ 19/02/2018፡- የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢንሳ) በተያዘው 2018 በጀት ዓመት በመጀመሪያ ሩብ ዓመት ውስጥ በተለያዩ ተቋማት ላይ 13,443 የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች መደረጋቸውን አስታወቀ።

የመከላከል አቅሙ 97.8 በመቶ መድረሱም ተገልጿል።ተቋሙ ይህንን የገለጸው የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድና የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት ነው።

የኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ትዕግሥት ሃሚድ በበኩላቸው፣ ተቋሙ የሳይበር ጥቃት የመከላከል አቅሙን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻሻለ በመምጣቱ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የመከላከል አቅሙ 97.8 በመቶ መድረሱን ተናግረዋል።

ቋሚ ኮሚቴው ሪፖርቱን ካዳመጠ በኋላ፣ 97.8 በመቶ የመከላከል ጥረት በጥንካሬ የሚወሰድ መሆኑን ጠቁሞ፤ ተቋሙ የመከላከል አቅሙን ከ99 በመቶ በላይ ከፍ ለማድረግ በትኩረት መሥራት እንደሚጠበቅበት አመላክቷል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates