
ኢትዮ ሞኒተር፡ 19/02/2018፡- የቻይና-አፍሪካ የአቃቤ ህግ የትብብር መድረክ ዛሬ በቻይና ጓንግዡ ግዛት የተጀመረ ሲሆን እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2025 ድረስ ይቀጥላል ሲል የኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ኢትዮጵያ በመድረኩ ላይ በፍትህ ሚኒስትር ሃና አራያሴላሴ የሚመራ ልዑክ እንደተወከለችም መረጃው አክሏል።
ልዑኩ በቻይና እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል የክስ ትብብርን ለማጠናከር በሚያተኩሩ የተለያዩ ስብሰባዎች ላይ እንደሚሳተፍ ይጠበቃል።
ከመድረኩ በፊት ሚኒስትር ሃና ከቻይና ህዝባዊ ሪፐብሊክ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዪንግ ዮንግ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸው ተገልጿል።



