የተለያዩ

የሰንደቅ ዓላማ ቀን በዛሬ ዕለት ተከበረ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 03/02/2018፡- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሠንደቅ ዓላማ ቀን እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር፣ ክብር እና ቃል ኪዳን የሚያድስበት ነው ሲሉ ተናገሩ።

18ኛው ብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን “ሠንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብስራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዐላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ህዳሴ!” በሚል መሪ ሀሳብ በተለያዩ አከባቢዎች ተከበረ።

የቀኑን አከባበር አስመልክቶ የኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት “ሠንደቅ ዓላማ የአንድ ሀገር መንግሥትና ሕዝብ ሉዓላዊነት፣ የፖለቲካ ሥልጣን፣ ነፃነት፣ ዕድገትና ማሕበረሰባዊ ትስስር መፍጠሪያ መሣሪያ ነው” በሚል ርእስ ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ሠንደቅ ዓላማ በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ የታተመ የሀገራዊ አንድነትና ነፃነት መገለጫ ታላቅ የብሔራዊ ኩራት አርማ መሆኑን አመላክቷዓል።

“የአንድነታችንና የሕብረታችን ማሳያ፣ ጀግኖች አያቶቻችን  ወራሪዎችን አሸንፈው ለመላው የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ምልክት የሆነውን ሠንደቅ ዓላማ የሕይዎት መስዋዕትን ከፍለው ለአዲሱ ትውልድ አስረክበዋል” ያለው መግለጫው፤ ይህንኑ መሠረት በማድረግ ሠንደቅ ዓላማ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ቦታ ተሰጥቶት የሚከበር ታላቅ ሀገራዊ በዓል መሆኑን አብራርቷዓል።

በመሆኑም የሀገራችንን ሠንደቅ ዓላማ ክብርና ተገቢውን ከፍታ አስጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ታላቅ ሀገራዊ ኃላፊነት መሆኑን የገለጸው ምክር ቤቱ፤ የብሔራዊ የሠንደቅ ዓላማ ቀን በሠንደቅ ዓላማ በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 863/2006  አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ መጀመሪያ ሳምንት ሰኞ እንደሚከበር መደንገጉን ገልጿል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates