አፍሪካ

የውጭ ቅጥረኞች የሱዳኑ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይል ሲደግፉ የሚያሳይ ምስል ወጣ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 26/01/2018፡- በየተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የሚደገፉ መሆናቸው የተነገረላቸው፡ የውጭ ሐይሎች በኤል ፋሸር ከተማ በጦርነቱ የተጎዱ የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ማሊሻዎች ሲያክሙ የሚያሳይ ቪዲዮ ተሰራጭቷል።

በኤል ፋሸር ከሚገኘው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ ከሚደገፈው የፈጣን ድጋፍ ሚሊሻ (ጃንጃዊድ) ለቆሰለ ተዋጊ የውጭ ሰዎች የመጀመሪያ እርዳታ ሲያደርጉ የሚያሳይ በቅርቡ የተሰራጨ ቪዲዮ በመላ ሱዳን ቁጣን መቀስቀሱን ተገልጿል።

ምስሉ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ በሱዳን ጦርነት ውስጥ ያላትን ሰፊ ተሳትፎ የሚያሳይ ነው ተብሏል።

እነዚህ በቆዳ ቀለማቸው ነጮች የሆኑት ሰዎች የሱዳን ዜግነት የሌላቸው እና ቅጥረኞች ስለመሆናቸው ታዛቢዎች እና ወታደራዊ ምንጮች አረጋግጠዋል።

ይህም በኮሎምቢያ ላሲላ ቫቺያ በተባለው የምርመራ ተቋም ካወጣው ማስረጃ ጋር ይዛመዳል ብሏል።

ተቋሙ እንደገለፀው በመቶዎች የሚቆጠሩ የኮሎምቢያ የቀድሞ ወታደሮች በአሳሳች ኮንትራት እንዴት እንደተመለመሉ፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ በኩል እንደተጓዙ እና በኋላም በሊቢያ በኩል ወደ ሱዳን እንደገቡ የሚያሳይ ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates