መካከለኛ ምስራቅ

እስራኤል በሁለት ዓመታት ጦርነት 1,152 ወታደሮች እንደተገደሉባት አስታወቀች።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 26/01/2018፡- ከጥቅምት 7 ቀን 2023 ጀምሮ 1,152 ወታደሮች መገደላቸውን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ አስታዎቋል።

ከእነዚህ ከ40% በላይ የሚሆኑት ከ21 ዓመት በታች የሆኑ እና የግዴታ ወታደራዊ አገልግሎታቸውን ሲፈጽሙ እንደነበር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ከሟቾቹ መካከል 141 ያህሉ ከ40 ዓመት በላይ የሆናቸው ሲሆኑ፣ ከሟቾቹ መካከል አብዛኞቹ ተጠባባቂ፣ አገልግሎታቸውን ያራዘሙ ወታደሮች ወይም ከግዳጅ እድሜ በላይ ያገለገሉ ናቸው ብሏል።

እንደ እየሩሳሌም ፖስት ዘገባ ከሆነ “እስራኤል የምትዋጋባቸውን ሁሉንም ግንባሮች እንዲሁም ከሀገሪቱ ደህንነት ጋር የተገናኘ እያንዳንዱን ክፍል ማለትም የአገሪቱ ወታደሮችን፣ የእስራኤል ፖሊስን፣ የእስራኤል ደህንነት ኤጀንሲን፣ የልዩ ኦፕሬሽን ሃይሎችን እና የዝግጅቱን ቡድን አባላትን ጨምሮ” ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates