አፍሪካ
ባለፈው ወር በተከበበችው ዳርፉር ከተማ በትንሹ 91 ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 23/01/2018፡- በሱዳን በተከበበችው ኤል ፋሸር ከተማ ባለፈው ወር በ10 ቀናት ብቻ ፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይሉ ወይም RSF ባደረሰው ጥቃት ቢያንስ 91 ንፁሀን ዜጎች መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።
ከተማዋን ለመቆጣጠር በሚፈልጉ ወታደሮች እና በተቀናቃኝ ኃይሎች መካከል በተካሄደው የተጠናከረ ጦርነት ውስጥ የተፈጸሙት ተከታታይ ጥቃቶች መሆናቸውም ድርጅቱ ገልጿል።
የዓለም ጤና ድርጅት እንደገለጸው ጦርነቱ በትንሹ 40,000 ሰዎችን ገድሏል፣ 12 ሚሊዮን የሚደርሱ ሌሎች ደግሞ ተፈናቅለዋል። የዓለም የምግብ ፕሮግራም እንደገለጸው ከ24 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ለከፋ የምግብ ዋስትና እጦት ተዳርገዋል።