አፍሪካ

ጅቡቲ በሶማሊያ ከአልሸባብ ጋር የምታደርገውን ጦርነት ለመደገፍ ተጨማሪ ጦር ልታሰማራ መሆኑ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 21/01/2018፡- ጅቡቲ በቀጣናው ሰላም እና ደኅንነት ውስጥ የረዥም ጊዜ ሚናዋን በማረጋገጥ የአልሸባብን የማያቋርጥ ስጋት ለመቋቋም ትላንት ተጨማሪ ወታደር ወደ ሶማሊያ ለመላክ ቃል ገብታለች ሲል ሂራን ኦንላይን ዘግቧል።

በተባበሩት መንግስታት የጅቡቲ ቋሚ ተወካይ ሞሃመድ ሲያድ ዶዋሌህ ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ይህን አቋም ማሳወቃቸውም መረጃው ጠቁሟል።

ሶማሊያ በመንግስት ግንባታ እና በፀጥታ ላይ እያስመዘገበች ያለውን እድገት ሀገራቸው እንደምትቀበል ገልፀው ነገር ግን አሁንም ትልቅ ፈተናዎች እንዳሉ አስጠንቅቀዋል።

እንደ ጥረቱ አካል ጅቡቲ እና ሶማሊያ ተጨማሪ የጅቡቲ ወታደሮችን ለማሰማራት የሚያስችል አዲስ የሁለትዮሽ ስምምነት መፈራረማቸውም አስታውቋል።

ሰራዊቱ በአልሸባብ ላይ እየተካሄደ ያለውን ዘመቻ ያጠናክራል ያሉት ተወካዩ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እና ማረጋጋት ተልዕኮ (AUSSOM) ስር የሚደረገውን የማረጋጋት ስራም ጅቡቲ እንደምትደግፍ አረጋግጧል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates