
ኢትዮ ሞኒተር፡ 19/01/2018፡- የኤርትራ ልዑካን በተመድ ጠቅላላ ጉባኤ እየተሳተፈ ይገኛል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ የተመራው የኤርትራ የልዑካን ቡድን በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካዎ ፕሬዚዳንት አማካሪን ጨምሮ ከተለያዩ መሪዎች ጋር መወያየቱ ተገልጿል።
በኒውዮርክ ይገኛሉ ተብሎ የተጠበቁት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ደግሞ ወደ ሞስኮ ተጉዘው ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተወያይተዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ኤርትራ እና ኢትዮጵያ በጉባኤው በባህር በር ጉዳይ ላይ ሃሳባቸውን ማቅረባቸው ተዘግቧል።
በፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ የተመራው የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ለጉባኤው እንዳብራራው ኢትዮጵያ የባህር በር እንደሚያስፈልጋት ይህም በአለም አቀፍ ህግ የተፈቀደ እንደሆነ ነው።
የባህር በር የሌላቸው አገሮች በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እየተጎዱ እንደሆኑ በመግለፅ በተለይ እንደ ኢ/ያ በማደግ ላይ ያሉ አገሮች ጉዳቱ የከፋ እንደሚያደርገው ተገልጿል።
ኤርትራ ግን የትኛውም ሀገር በወደቧ ላይ የባህር ሃይል እንዲገነባ እንደማትፈቅድ በግልፅ ተናግራለች።
የኤርትራው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳሌህ ኤርትራ የትኛውም ሀገር ጦሯን በወደብ ላይ እንዲያሰማራ እንደማትፈቅድ እና የሉዓላዊነት ጥሰት ነው ብሎቷል።
ጎረቤት ሀገራት ወደቦቼን በአለም አቀፍ ህግ እንጂ በኃይልና በማስፈራራት ሊጠቀሙበት አይችሉም ብላለች ኤርትራ።
“የወደቦችን አጠቃቀም የንግድ ጉዳይ እንጂ የፖለቲካ ወይም የወታደራዊ ጉዳይ አይደለም” ያሉት ሚኒስትሩ፣ የባህር ወደብ ያላቸው ሀገራት ከጎረቤቶቻቸው ጋር ተባብረው የልማት አጋር እንዲሆኑ የሚጠበቅባቸው በአለም አቀፍ ህግ፣ ሉዓላዊነት ማክበር እና ጣልቃ አለመግባባቶችን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ገልጿል።
እውነተኛ ትብብር በማስፈራራት ሳይሆን በመተማመን ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት ያሉት ሚኒስትሩ “ኤርትራ ሉዓላዊት ሀገር ነች፣ ሉዓላዊ የባህር ዳርቻ ያላት ወደቦቿም ብሄራዊ ሃብቶቿ ናቸው” ሲሉ ተደምጧል።
ኤርትራ የትኛውም የውጭ ወታደራዊም ሆነ የባህር ሃይል ወደቦቿ እንዲጠቀም እንደማትፈቅድ ገልጻ፣ የወደብ አጠቃቀምን በተመለከተ ማንኛውም ጉዳይ የሚወሰነው በኤርትራ እና በመረጠቻቸው አጋሮቿ መካከል በሚደረጉ የሁለትዮሽ ስምምነት ነው።
ቀይ ባህርን በድርድር አለበለዚያም በሐይል እይዛለሁ የምትለው ኢትዮጵያ ግን የባህር ሃይል አሰልጥና በመጠባበቅ ትገኛለች።
ሁለቱም ከገሮች በዚህ እሰጣ ገባ ባሉበት ወቅት አሜሪካ እና ሩሲያ ለመደራደር እንቅስቃሴ መጀመራቸውን ተነግሯል።
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ መጀመሪያ በሩስያ ቀጥሎም በአሜሪካ እንደሚገናኙ የወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።
ባለፈው ሳምንት ኤርትራ በቀይ ባህር ጉዳይ ከኢትዮጵያ ለመደራደር ዝግጁ መሆኗ ገለፀች የሚል ዜና በስፋት ቢሰራጭም በኢትዮጵያና በአፍሪካ ሕብረት የኤርትራ ጉዳይ አስፈፃሚ አቶ ቢኒያም በርሀ ዜናው ሐሰቶ መሆኑ ገልጿል።
“ኤርትራ በሉአላዊነቷ ከማንም አገር አልተወያየችም፣ በመሬቷ፣ በባህሯ እና ሰማይዋ አሁንም ከሚልዮን ዓመት በኃላም አትወያይም” በማለት በx ገፃቸው አስፍሯል።
አሁን እየወጡ ያሉት መረጃዎች እንደሚያሳዩት ደግሞ ሁለቱም አገሮች ለድርድር ሞስኮና ዋሽንግተን ሊቀመጡ እንደሚችሉ ነው።