ኢትዮጵያ

የአሜሪካ ኤምባሲ አሜሪካውያን የ ኢትዮጵያን የኢሚግሬሽን ህግ እንዲያከብሩ አሳሰበ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 14/01/2018፡- አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ወይም የሚጎበኙ አሜሪካውያን የሀገሪቱን የኢሚግሬሽን ህጎችን በጥብቅ እንዲያከብሩ አሳሰቡ።

አምባሳደሩ በኤምባሲው በኩል ትናንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ በኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን ፖሊሲ ላይ የተደረገውን ለውጥ በመጥቀስ፤ አሜሪካውያን በኢትዮጵያ ቆይታቸውን የሚመሩ ህጎችን ማወቅና መዘጋጀት እንዳለባቸውና ህጉን ማክበር ወሳኝ ጠቀሜታ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ማሲንጋ በህዳር 2017 የኢትዮጵያ መንግስት ህገወጥ ስደትን ለመቀነስ የቪዛ ጊዜ ላሳለፈ ሰው የሚጣልበትን የገንዘብ ቅጣት በቀን ወደ 30 የአሜሪካ ዶላር አሳድጓል ብለዋል። ይህ ቅጣት በፍጥነት ሊከማች የሚችል ነው ሲሉ ጠቅሰዋል።

አምባሳደር ማሲንጋ የኢትዮጵያ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት “ቪዛ አሳልፎ በመቆየት የገንዘብ ቅጣት ያለባቸውን የአሜሪካ ዜጎች ዕዳቸውን ሙሉ በሙሉ በዶላር እስኪከፍሉ ድረስ ከአገር እንዳይወጡ ሊከለክሉ እንደሚችሉ” አስጠንቅቀዋል። በተጨማሪም የአሜሪካ ኤምባሲ ይህንን ቅጣት ለመክፈል ብድር የመስጠት ፍቃድ እንደሌለው አብራርተዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates