የተለያዩ
የተመድ ሥርዓትንና መዋቅር 21ኛው ክፍለ ዘመንን በሚመጥን መልክ መለወጥ የሚገባ መሆኑን ዋና ጸሐፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 14/01/2018፡- የተመድ ሥርዓትንና መዋቅር 21ኛው ክፍለ ዘመንን በሚመጥን መልክ መለወጥ የሚገባ መሆኑን ዋና ጸሐፊው አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ዛሬ በይፋ በተከፈተው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 80ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ገለጹ።
በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉቴሬዝ፤ “ዓለማችን በተለያዮ ሠላምና ፀጥታ ጉዳዮች፣ ድህነት፣ ረሀብ፣ ጦርነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ የኢኮኖሚ ቀውስ እየተፈተነች ባለበት ወቅት የሚከበረው የተመድ 80ኛ ዓመት፤ አባል ሀገራት ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለች ዓለም ለመፍጠር በጋራ መሥራት ይገባቸዋል” ብለዋል።
ከእነዚህ ሥራዎች መካከል አንደኛው የተባበሩት መንግሥታት ሥርዓትና መዋቅርን 21ኛው ክፍለ ዘመን በሚመጥን መልክ መለወጥ የሚገባ መሆኑንም ዋና ጸሐፊው ገልጸዋል።
ለዚህም የዓለም ኀብረተሰብ ምርጫውን ሠላም፣ ፍትህ፣ ዘላቂ ልማት እና ሰብአዊ ክብር ላይ ሊያደርግ የሚገባው መሆኑንና ለተግባራዊነቱም ቁርጠኝነት እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያም በኘሬዝዳንት ታየ አፅቀሥላሴ የተመራ ልዑካን ቡድን አማካኝነት በጉባኤው ላይ ተሳትፎ እያደረገች እንደምትገኝ ከውጭ ጉዳእ ሚንስቴር የተገኘነ መረጃ ያመላክታል።