እስካሁን 151 የዓለም አገሮች የፍልስጤም አገርነት እውቅና ሰጡ።
"የፍልስጤም ሃገርነት መብት እንጂ ስጦታ አይደለም" አሉ የተመድ ዋና ፀሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 13/01/2018፡- በኒዮውርክ እየተካሄደ በሚገኘው የተመድ 80ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ሐያላን ሀገራትን ጨምሮ ከአፍሪካ እስከ ኤስያ፣ ከአውሮፓ እስከ ሰሜንና ላቲን አሜሪካ በርካታ አገሮች የፍልስጤም አገርነትን እውቅና እየሰጡ ይገኛሉ።
ምናልባትም ይህ ሰዓት ዓለም ዳግም ታሪክ የምትሰራበት፣ አሜሪካና እስራኤል ዲፕሎማሲያዊ ሽንፈት የሚያስተናግዱበት እንደሚሆን ብዙዎች በጉጉት እየጠበቁት ነው።
የአሜሪካ ሸሪኮች የነበሩ አገሮች ሳይቀሩ ይህን እርምጃ መውሰዳቸው ደግሞ ልዩ እንደሚያደርገው ተንታኞች እየተናገሩ ይገኛሉ።
ፈረንሣይ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና ስትሰጥ “በወረራ የተያዙባትን አከባቢዎች ጨምሮ እንደሚሆን” አስታወቃለች።
ፈረንሣይ ትላንት መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም አመሻሽ ላይ በይፋ ለፍልስጤም የሀገርነት እውቅና ስትሰጥ “በ1967ቱ ሶስተኛው የአረብ-እስራኤል ጦርነት ወቅት በወረራ የተያዙባትን አከባቢዎች ያካተተ እንደሚሆን” በኢትዮጵያ የፈረንሣይ አምባሳደር አሌክሲስ ላሜክ ተናገሯል።
አምባሳደሩ ይሄን ያስታወቁት ትላንት መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም የፍልስጤም አገርነት እውቅናን በተመለከተ የፈረንሣይ መንግስት ባወጣው መግለጫ ዙርያ ለመገናኛ ብዙኃን ማብራርያ በሰጡበት ወቅት ነው።
አሌክሲስ ላሜክ በዚሁ ወቅት “ዛሬ የምናየው ፈረንሣይ ለፍልስጤም አገርነት እውቅና መስጠቷ፤ ከዘጠኝ ወራት በፊት፣ ፈረንሣይ ከሳኡዲ አረቢያ ጋር በመሆን የእስራኤል እና ፍልስጤም ግጭትን ለመቋጨት የሁለት ሀገርነትን መፍትሔ ለመጀመር የታለመ ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው” ሲሉ ተናግረዋል።
ፈረንሳይ ከስድስት ተጨማሪ ሀገራት መካከል የፍልስጤም ሀገርነትን በይፋ እውቅና ስትሰጥ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የፍልስጤም ሀገርነት እውቅና ስንሰጥ የእስራኤላዊያን ህልውና እየነፈግን አይደለም ብሏል።
አንዶራ፣ ቤልጂየም፣ ሉክሰምበርግ፣ ማልታ፣ ሞናኮ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ሌሎች በርካታ አገሮች እውቅናውን ተቀላቅሏል።
ለፍልስጤም ዕውቅና የሰጡ ተጨማሪ አገሮች ከ193 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባል ሀገራት መካከል 151 የሚያህሉትን እውቅና ሰጥቷል።
ይህ ማለት በአሁኑ ጊዜ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የፍልስጤምን ግዛት እውቅና ሰጥቷል።
የተመድ ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ “የፍልስጤም የአገርነት እውቅና መብት እንጂ ስጦታ አይደለም፤ የሐማስ ጥቃትም በፍልስጤም ህዝቦች የሚፈፀም የጅምላ ቅጣትም ተቀባይነት የለውም” በማለት የሁለት አገሮች የሰላም ሐሳብ ብቸኛ የችግሩ መፍትሄ መሆኑ ተናግሯል።
የቱርኪው ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጠይብ ኤርዶጓን “በአንድ ወቅት የሆሎኮስት ሰለባ የነበረ የእስራኤል መንግስት እንዴት በጎረቤቱ ላይ ጄኖሳይድ ይፈፅማል”? በማለት ጠይቋል።
አሁን አብዛኞቹ አገሮች የፍልስጤም እውቅና ቢሰጡም እስራኤልና አሜሪካ ውሳኔውን እየተቃወሙት ይገኛሉ።
እንደነ ጣሊያን የመሳሰሉ አገሮችም እስካሁን ያልወሰኑ አገሮች ናቸው።
ለእስራኤል የጦር መሳሪያ ይሸጣል ተብሎ የምትታማው የጣሊያን መንግስት እስካሁን ለፍልስጤም አገርነት እውቅና ባለመስጠቱ ዜጎቹን አስቆጥቷል።
በ75 የጣልያን ከተሞች ከ80 ሺ የሚበልጡ ዜጎች ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ እያደረጉ ይገኛሉ። የጣሊያን መንግስት ለእስራኤል የሚያደርገው ድጋፍ እንድያቆምና የፍልስጤም አገርነትን እውቅና እንዲሰጥ ዜጎቹ ጠይቋል። ሰላማዊ ሰልፉ ቆይቶ ወደ ህዝባዊ ዓመፅ መለወጡ ሚድያዎች እየዘገቡት ነው።
ብተመሳሳይ በስፔይንም ሺዎች የተሳተፉበት ህዝባዊ ሰልፍ በማካሄድ የስፔይን መንግስት የእውቅና ውሳኔውን እንዲቀላቀል ጊፉት እያደረጉ ነው።
እስካሁን የፍልስጤም አገርነትን ኬልደገፉ 42 አገሮች ከአፍሪካ ኤርትራና ካሜሮን እንደሚገኙበት እየተገለፀ ይገኛል። ኢትዮጵያም በይፋ ያለችው ነገር የለም።
አገሮች የፍልስጤም አገርነት እውቅና እየሰጡ በሚገኙበት በዚህ ወቅት እስራኤል በጋዛ የተጠናከረ ጥቃት እያደረገች ትገኛለች።
መረጄዎች እንደሚያሳዩት ወደ 68 ሺ የሚጠጉ ፍልስጤማዊያን ሞቷል። ይህ አሃዝ 1/3 ኛ የፍልስጤም ህዝብ ማለት ነው።