አፍሪካ

የአፍሪካ ህብረት በሱዳን ያለውን ሁኔታ በሊቢያ የሆነውን እንዳይደገም በጄኔራል አል ቡርሃን ከሚመራው የሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት ጋር እሰራለሁ ሲል አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 09/01/2018፡- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ማሃሙድ አሊ የሱፍ  እንዳሉት “የአፍሪካ ችግሮች በአፍሪካዊ መፍትሄዎች ሊፈቱ ይገባል” ሲሉ ህብረቱ ቀውሱን ለመቅረፍ የሚረዱትን የውጭ ሽምግልና ወይም አቅርቦቶችን እንደማይቀበል ጠቁመዋል።

በውይይቱ ወቅት ጠያቂው “በፖርት ሱዳን ውስጥ በጦር ኃይሎች የሚደገፍ አስተዳደር” ከ “ፈጣን ደጋፊ ሚሊሻዎች እራሱን የሚገልጽ ባለስልጣን” መኖሩ ሱዳንን የረዥም ጊዜ የመበታተን አደጋ ላይ ይጥላል ወይ ሲል ጠይቋል።

የዩሱፍ ምላሽ “ይህ ስጋት ገና ከጅምሩ ነበር፣ የአፍሪካ ህብረትም የሊቢያው ሁኔታ በሱዳን እንዲደገም አይፈልግም” ሲለ አጽንኦት ሰጥቷል።

የአፍሪካ ኅብረት አቋም ግልጽ ነው፡ በጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን መሪነት ከሽግግር ሉዓላዊነት ምክር ቤት ጋር ተባብሮ መስራቱን በመቀጠል፣ ሱዳን የምትፈልገውን ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ለማሳካት ያለመ የፖለቲካ እና ወታደራዊ ኃይሎችን በሱዳን የሚመራ ውይይት ለማድረግ እያሰበ ነው ብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates