አሜሪካኢትዮጵያ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከፍተኛ አማካሪ ማሳድ ቡሎስ መወያየታቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 08/01/2018፡- ማሳድ ቡሎስ በx ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት፦ “ዛሬ በአዲስ አበባ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በመገናኘቴና በሀገሮቻችን መካከል ያለውን ዘላቂ አጋርነት በድጋሚ በማረጋገጣችን ክብር ይሰማኛል ብሏል።

የኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር ያለው ግንኙነት አስፈላጊነት እና የፕሬዝዳንት ትራምፕ ቁልፍ ቅድሚያ የሆነውን የሰላም እና የቀጠናውን መረጋጋት በማስፈን ረገድ ያላትን ሚና አጽንኦት ሰጥተንበታል ሲሉም ፅፏል።

በተጨማሪም በአሜሪካ እና በኢትዮጵያ መካከል የጋራ ብልጽግናን በሚያስገኙ የተለያዩ የንግድ እድሎች ላይ መወያየታቸው ገልጿል።

ምንም እንኳን የትዊተር (x) መልዕክቱ አጠቃላይ እና ወዳጃዊ ቢመስልም፣ ተንታኞች ከበስተጀርባው ጠንካራ የአሜሪካን አቋም የሚያንጸባርቅ ነው ሲሉ ይገልፃሉ።

“የኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር ያለው ግንኙነት አስፈላጊነት” የሚለውን የቡሎስ ፅሑፍ በቀጥታ የሚያመለክተው የኢትዮጵያ የ”ቀይ ባህር” ጥያቄ ምክንያት ከኤርትራ ጋር የተፈጠረውን ውጥረት “በንግግር ፍታ” የሚል ጠንካራ መልዕክት ያለው መሆኑ የዲፕሎማሲ ባለሞያዎች ይናገራሉ።

ይህ የኃይል አማራጭን ለማሰብ ለሚደረግ ማንኛውም ሙከራ የተሰጠ የማስጠንቀቂያ ደወል ነውም ይላሉ።

“የሰላም እና የቀጠናውን መረጋጋት በማስፈን” የሚለው አባባልም አሜሪካ ከኢትዮጵያ የምትጠብቀው ሚና በቀጠናው ውስጥ ሰላምን ማስፈን መሆኑን ያስገነዝባል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከኢትዮጵያ ሲሰሙ የነበሩት “በኃይልም ቢሆን” የሚሉ ንግግሮች ከዚህ ሚና ጋር የሚጋጩ በመሆናቸውም ዋሽንግተን ኢትዮጵያ ወደ ቀድሞው “ሰላም አስከባሪ” ሚናዋ እንድትመለስ ግፊት እያደረገች መሆኑን ያሳያል የሚሉ አሉ።

ይኸውም የጉብኝቱ ዋነኛ አላማ የኢትዮጵያን የ”ቀይ ባህር” ጥያቄ ተከትሎ የመጣውን ውጥረት ማብረድ እና አዲስ አበባ የኃይል አማራጭን እንዳታስብ ጠንካራ መልዕክት ማስተላለፍ መሆኑን እየተገለፀ ይገኛል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates