ኢትዮጵያ

“የባህር በር የማይቀር ጉዳይ በመሆኑ ኤርትራዊያን ለድርድር ተዘጋጁ” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ(ዶ/ር) ተናገሩ።

" ኢትዮጵያ የመውጫና መግቢያ በሯን ማበጀቷ አይቀሬ ነው " ሳሉም አክሏል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 08/01/2018፡- “ዛሬ የኛ የሆነውን ቀይ ባህር መልሶ ለመጠየቅ የሚሰጋ ፣ የሚጠራጠር ትውልድ መፈጠሩ የስነልቦና ስብራት አካል ነው፤ አንችልም ብሎ ነው የሚያስበው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ኢትዮጵያ የሚያልክ ሀገር የባህር በር ሳይኖራት ለልጆቻችን መሸጋገር አለበት ብሎ ማመን ተገቢ እሳቤ አይደለም ብሏል።

“ይሄን ለማሳካት ውጊያ፣ ግጭት ያስፈልጋል ብለን አናምንም፤ ለዚህም ነው ለ5 ዓመትታ ስንለማመጥ የነበረው ” ሲሉም አክሏል።

” አሁንም በሰላም በዓለም ህግ መሰረት ኢትዮጵያን ከዘጋት በር እና ድሃ ካስባላት መጠሪያዋ መገላገል አለባት ብለን ስለምናምን በየትኛውም መድረክ ከኢትዮጵያ ጋር በሰላማዊ መንገድ ለመነጋገር የሚፈቅድ አካል ካለ እጃችን ከምን ጊዜውም በላይ የተዘረጋ ነው ” ሲሉ ተናግረዋል።

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ” ኢትዮጵያ የጂዮግራፊ እስረኛ ሆና ለዘላለም ትኖራለች ብሎ የሚያስብ ኢትዮጵያዊ  ካለ እርሱ የሞተ ነው ፤ ሰላም ታስቀድማለች ድህነትን ትፋለማለች መውጫ መግቢያ በሯን ታበጃለች ይህ አይቀሬ ጉዳይ መሆኑን ተገንዘበው ወንድም እህቶቻችን በፈጠነ ጊዜ ለድርድር እራሳቸውን ዝግጁ ማድረግ አለባቸው ” ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates