ፖለቲካ

“ከረጅም ጊዜ እውቀት አጠር ትንተና ዘመን በኋላ ወደዚህ እውቀት ተኮር ትንተና በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ”  ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ ተናገሩ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 07/01/2018፡- አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በተመረቀው የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መፅሀፍ ላይ ሂሳዊ ዳሰሳ እንዲያቀርቡ በተጋበዙበት ወቅት ‹‹ከረጅም ጊዜ እውቀት አጠር ትንተና ዘመን በኋላ ወደዚህ እውቀት ተኮር ትንተና በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ›› በማለት ንግግራውን ጀምረዋል፡፡

ሲቀጥሉም መፅሀፉን ‹‹ከመጀመሪያ እስከመጨረሻ አገሪቱ አላት የሚላትን ችግሮች የዳሰሰ፣ ከዚያም የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የጠቆመ ዝርዝር የዳሰሰ በመሆኑ ጊዜ ወስደን ልንነጋገርበት የሚገባ ትልቅ ዶክመንት ነው›› በማለት አስታውቀዋል፡፡

አቶ ጌታቸው የመጀመሪያውን መደመር መፅሀፍ ማንበባቸውን አውስተው ያነበቡትም ‹‹አቃቂር ለማውጣት›› እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

በተፈጠረው ችግር ሁለተኛውና ሶስተኛው መፅሀፍ እንዳላነበቡት የተናገሩት አቶ ጌታቸው  ‹‹በ40 አመቱ ግለ ታሪክ ፅፎ አገር አስተምራለሁ የሚል ሰው ባለበት አገር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንኳንም ግለ ታሪክ አልፃፉ፡፡ እንኳንም ሀሳብ ተኮር መፅሀፍ ፃፉ›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡

“አንዳንዶቻችን ፍሬሽማን ሆነን ድራፍት የጀመርንበት እና ከፊል ጭቃ የነበሩ ቤቶች ፈርሰው፣ ወደ ህንፃዎች እና ቤተመጻሕፍት ስለ ተቀየሩ አዲስ አበባ ውስጥ ቅርሶች እየፈረሱ ነው ብለን እናለቅሳለን። ለምሳሌ አንዱ ድራፍት ቤት ወደ አብርሆት ቤተመጽሐፍት ተቀይሯል” ሲሉም አቶ ጌታቸው ተናግሯል።

ስለቤተ መንግስት ግንባታው ሲናገሩም “ለምን አይቀርበትም ይል ነበር፤ በአካል ከተመለከቱ በኃላ ግን አንድ ከተማ እየተገነባ ያለው” ብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates