ኢትዮጵያ

ሶማሊያ የኢትዮጵያ ሕጋዊ የባህር በር ጥያቄ እንደምትደገፍ አስታወቀች።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 07/01/2018፡- “ኢትዮጵያ የባህር በር ፍለጋዋን በዓለም አቀፍ ሕግ ማዕቀፍ ውስጥ እንድታደርግ እንጠብቃለን” ሲሉ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ ገልጿል።

የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ፣ ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የባህር በር የማግኘት ፍላጎቷን በዓለም አቀፍ ሕጎችና ስምምነቶች መሠረት እንድታስቀጥል ድጋፋቸውን ገለጹ።

ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት ከ“አል አረቢያ” የዜና ጣቢያ ጋር በቅርቡ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

ፕሬዝዳንቱ በቃለ ምልልሳቸው፣ የኢትዮጵያ የባህር በር ፍለጋ “በዓለም አቀፍ ሕግ ማዕቀፍ ውስጥ አዲስ አይደለም” ሲሉ አብራርተዋል።

ማንኛውም ሀገር ጥቅሙን ለማስጠበቅ ዓለም አቀፍ ሕጎችን እስካከበረ ድረስ ሊጠቀምባቸው የሚችላቸው እውቅና ያላቸው ዘዴዎችና አካሄዶች እንዳሉ ገልጸዋል።

“ኢትዮጵያ በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ጥረቷን የምታደርግ ከሆነ፣ ይህንን ለማሳካት እንደምትችል ተስፋ አለን” ብለዋል።

የሶማሊያ አቋም ጽኑና ግልጽ እንደሆነ የገለጹት ፕሬዝዳንቱ፣ በአካባቢው ያሉ አለመግባባቶች በውይይት፣ በመደራደርና መግባባትን በመከተል መፈታት እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።

ይህ መግለጫ ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ቀይ ባህር ላይ የባህር ኃይል ጣቢያ ለመመስረት የፈረመችውን ስምምነት ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ የመጣ ነው።

ሶማሊያ ይህንን ስምምነት ሉዓላዊነቷን የጣሰ ድርጊት አድርጋ ትቆጥራለች።

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ፣ በቀይ ባህር አዋሳኝ ሀገሮች መካከል ለጋራ ጥቅም የሚውል መረጋጋትን ለመፍጠር ውይይት፣ መግባባትና ትብብር እንዲደረግ ጠይቀዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates