መካከለኛ ምስራቅ
የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ የሶማሊያ መንግስትን፣ የፑንትላንድን እና የጁባላንድ መሪዎችን የፖለቲካ አለመግባባቶችን ለመፍታት እየሸመገለች መሆኑን ተሰማ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 06/01/2018፡- ከተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የሶማሊያ ፌዴራል መንግስት፣ የፑንትላንድ እና የጁባላንድ ክልላዊ መንግስታት መሪዎችን በማሰባሰብ ለረጅም ጊዜ የቆየውን የፖለቲካ አለመግባባት ለመፍታት እየተሰራ ነው።
የጁባላንድ ፕሬዚዳንት አህመድ መሀመድ እስላም (አህመድ ማዶቤ) እና የፑንትላንድ ፕሬዝዳንት ሰኢድ አብዱላሂ ዴኒ በተባበሩት አረብ ኢምሬትስ እንደሚገኙ መረጃዎች ጠቁሟል።
የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ በድርድሩ ላይ የሽምግልና ሚና እየተጫወተች ሲሆን፥ ይህም ለዓመታት የዘለቀውን ግጭት ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት በማቀድ መሆኑን ተገልጿል።
ያልተረጋገጡ ዘገባዎች እንደሚያመለክቱት የሶማሊያ ፌዴራላዊ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በኳታር በተካሄደው የእስላማዊ እና የአረብ ሀገራት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ተሳትፎቸውን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ እንደሚሄዱ ይጠበቃል።
አለመግባባቱ የህገ መንግስት ማሻሻያዎችን፣ የምርጫ ሂደቶችን እና የመንግስት ተቋማት አስተዳደርን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው ተብሏል።