ኢትዮጵያየአየር ንብረት አካባቢ

አስከፊ የሆነውን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ለመዋጋት የለውጥ ርምጃ ያስፈልጋል አሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴ።

ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ሳምንት በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 28/12/2017፡- ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሞሐመድ አሊ ዩሱፍ ጨምሮ የሀገራትና የዓለም አቀፍ ተቋማት ኃላፊዎች በተገኙበት ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ሳምንት በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል።

በመድረኩ ላይ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እንዳሉት፤  አፍሪካ በዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ያላት ሚና አነስተኛ ቢሆንም በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ዋጋ እየከፈለች ነው።

በዚህም አፍሪካ ለታዳሽ ቴክኖሎጂ አስፈላጊ የሆኑ የተፈጥሮ ሀብቶች ያላት እንደመሆኗ በዓለም የአየር ንብረት ላይ የመሪነት ሚና መጫወት እንዳለባት አስገንዝበዋል።

ሁሉንም ያማከለ እና  ፍትሐዊ የሆነ  የአየር ንብረት ፖሊሲ እና የገንዘብ ድጋፍ እንዲተገበርም ጥሪ አቅርበዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ  በዓለም ላይ በተለይም በአፍሪካ የሚያደርሰው ተጽእኖ አስከፊ በመሆኑ የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት አስቸኳይ የለውጥ ርምጃ ያስፈልጋል ብለዋል።

አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል  የምትሰራቸውን ጅምር ልማቶችን ማፋጠን፣ የስራ ዕድል መፍጠር እና የምግብ ዋስትናን ማጎልበት እንደሚገባ አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብርን ጨምሮ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ጥረት እያደረገች እንደሆነ አንስተው፤ በዘንድሮ ክረምት ብቻ ከ7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ መሰራቱን ጠቅሰዋል።

ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2027 የሚካሄደውን የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የማስተናገድ ፍላጎት እና አቅም እንዳላት አመልክተዋል።

የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋም በቁርጠኝነት የምትሰራው ኢትዮጵያ በመስኩ ያከናወነቻቸውን ተግባራት የጉባኤው ተሳታፊዎች እንዲጎበኙም ግብዣ አቅርበዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates