አውሮፓአፍሪካ

እንግሊዝ በካይሮ የሚገኘው ኤምባሲዋን በጊዜያዊነት መዝጋቷ አስታወቀች።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 28/12/2017፡- ባሳለፍነው ሣምንት አንድ ግብጻዊ አክቲቪስት በእንግሊዝ መታሰሩን ተከትሎ በተፈጠረ ዲፕሎማሲያዊ ውዝግብ ምክንያት ዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) በካይሮ የሚገኘው ኤምቤሲዋ በጊዜያዊነት እንዲዘጋ ማድረጓን አስታወቀች።

በተለያዩ የአለም ሀገራት በሚገኙ የግብጽ ኤምባሲዎች በር ላይ የግብፅ መንግስት ወደጋዛ የሰብአዊ እርዳታ ለማስገባት እንዲቻል የራፋህ በርን እንዲከፍት የሚጠይቁ ሰልፎች ሲካሄዱ ሰንብተዋል።

ከነዚህም መካከል ባለፈው ሣምንትም ለንደን በሚገኘው የግብፅ ኤምባሲ በር ላይ የተካሄደው ሰልፍ አንዱ ሲሆን በወቅቱ የግብፅ መንግስት ቀንደኛ ደጋፊ የሆነ ግለሰብ ሠልፈኞችን ሲጋፈጥ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ ካይሮ በአፀፋው የእንግሊዝ ኤምባሲ የደህንነት መከላከያዎችን አንስታለች ተብሏል።

ግብፅ ለበርካታ አስርት አመታት በካይሮ የሚገኘውን የኢንግሊዝ ኤምባሲ ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል መከላከያ ማንሳቷ የተገለጸ ሲሆን፤ ይህንንም ተከትሎ የሚከሰተውን ተፅዕኖ ለመገምገም በሚል ኤምባሲው በጊዜያዊነት መዘጋቱን የእንግሊዝ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ቢሮ አመልክቷል።

የግብፅ ባለሥልጣናት በበኩላቸው ግብጽ የእርዳታ አቅርቦትን ከልክላለች መባሉን አስተባብለው እስከ ንብረት ማውደም ድረስ የተከሰተባቸውን አንዳንድ ሰልፎች በጽኑ አውግዘዋል።

በተጨማሪም ሰልፎቹ “በውጭ የሚኖሩ የግብፅ ወጣቶች ህብረት” የተሰኘ በመንግስት የሚደገፍ ቡድን እንዲመሰረት አድርጓል የተባለ ሲሆን ህብረቱ በግብጽ መንግሥት ላይ የሚደርስበትን ተቃውሞ በተቃረነ መልኩ ለግብጽ መንግስት ድጋፍ የሚያሳዩ ሰልፎችን ማካሄዱን የዘገበው ዘ ቴሌግራፍ ነው።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates