የተለያዩ
በትግራይ ክልል በትራፊክ አደጋ 42 ተጓዦች ሞትና ከባድ የአካል ጉዳት ደረሰባቸው።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 19/12/2017፡- ዛሬ ነሀሴ 19 ቀን 2017 ዓ.ም ንጋት 11:00 ሰዓት በትግራይ ማእከላዊ ዞን እንትጮ ከተማ አንድ የህዝብ ማመላለሽ ተሽከርካሪ በደረሰበት አደጋ 13 ተጓዦች ወድያውኑ ህይወታቸው ማለፉ ተገልጿል።
በ29 ተጓዦች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰ ሲሆን ወደ ገደል በገባችው አውቶቡስ ተሽከርካሪው የተጫነባቸው ሁለት ሰዎችን ለማውጣት የክሬን እገዛ ማስፈለጉን ተሰምቷል።
ፖሊስ የአደጋው መነሻ እየተጣራ እንደሆነ ነገለፀ ሲሆን አሽከርካሪዎች ሌሊት ባለመጓዝና አልኮል ጠጥቶ ባለማሽከርከር የትራፊክ አደጋ እንዲቀንሱ አሳስቧል።
ሆኖም መረጃዎች እንደሚጠቁሙት የአደጋው መነሻ ሽፍቶች በከፈቱት ተክስ መሆኑን ነው።
ከዚህ በፊትም በአከባቢው ተመሳሳይ አደጋ ኣጋጥሞ እንደነበር ይታወሳል።