ኢትዮጵያኢኮኖሚ

በትግራይ ፀለምቲ ወረዳ በተከሰተ ድርቅ ወደ 50,000 የሚጠጉ ሰዎች ለረሃብ አደጋ መጋለጣቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 13/12/2017፡- በሰሜን ምዕራብ በትግራይ ፀለምቲ ወረዳ በተከሰተው ከባድ ድርቅ ምክንያት ወደ 50,000 የሚጠጉ ሰዎች ለረሃብ እና ለመፈናቀል መጋለጣቸውንና ከ9,000 በላይ የሚሆኑ የቤት እንስሳት መሞታቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት ገልጿል።

የላዕለይ ፀለምቲ ወረዳ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ነጋ አዱኛ፤ “9,367 አባወራዎች ወይም 49,799 ሰዎች አደጋ ላይ ናቸው። አንዳንድ ሰዎች ምግብ ፍለጋ አካባቢውን ለቀው መውጣት ጀምረዋል ብሏል።

እስካሁን 807 ከብቶች፣ 8,351 በጎችና ፍየሎች፣ 108 አህዮች እና ሁለት ግመሎች በረሃብ ሞተዋል።

ገበሬዎች የቀሩትን እንስሳቶቻቸውን ለመታደግ ከአካባብው በመልቀቅ ላይ ናቸው።” ሲሉ ለክልሉ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።

አስተዳዳሪው አክለውም፤ በወረዳው ስድስት ቀበሌዎች በድርቁ ተጎድተዋል ብለዋል።

“እነዚህ አካባቢዎች ከዚህ ቀደም ድርቅ ተከስቶበት የነበረውን ቆላ ተምቤን የሚዋሰኑ ናቸው። በተለይም ሜዳ፣ ምድረ-ሐምሶ እና ደገረባይ የተባሉት ሦስት ወረዳዎች በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ” ሲሉ ገልጸዋል።

ተጨማሪ የሚከሰት የሕይወት መጥፋት እና ስደትን ለማስቀረት የፌዴራል መንግሥት እና ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች በአስቸኳይ እርዳታ እንዲያደርጉ አስተዳደሩ ጥሪ አቅርቧል።

የትግራይ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ገብረሕይወት ገብረእግዚአብሔር የድርቁን ያደረሰውን ጉዳት ለአዲስ ስታንዳርድ አረጋግጠዋል፤ ነገር ግን አሃዞችን ከመስጠት ተቆጥበዋል። “በድርቁ ላይ ክልል አቀፍ ጥናት እያደረግን ነው። ገና አልተጠናቀቀም” ብለዋል።

በማዕከላዊ ትግራይ ቆላ ተምቤን በተከሰተው ድርቅ ቢያንስ 22 ሰዎች እና ከ27,000 በላይ የቤት እንስሳት ህይወት አልፏል። የሞት መጠኑ ከፍ ማለቱ በክልሉ እየተፈጠረ ያለውን ሰብአዊ ቀውስ አመላካች መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የሚደረገው እርዳታ አነስተኛ መሆኑ ችግሩን አባብሶታል ተብሏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates