አፍሪካ

ጄኔራል አልብሩሀን ወታደራዊ ሹም ሽር አደረጉ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 13/12/2017፡- የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር የሆኑት ሌተና ጄኔራል አብዱል ፈታህ አልብሩሀን በጦር ሀይላቸው ውስጥ ከፍተኛ የሚባል ሹም ሽር ማድረጋቸውን አስታውቀዋል፡፡

በዚህ ሹም ሽር አብዛኛዎቹን የጦሩን አመራሮች በአዲስ ተክተዋቸዋል፡፡

በሌላ በኩል ከሱዳን ጦር ሀይል ጋር በትብብር ተሰልፈው ይዋጉ የነበሩ ሀይሎች መከላከያውን መቀላቀል እንደሚችሉ የሚገልፅ አዲስ አዋጅ አውጥተዋል፡፡

በተለያዩ ግዛቶች በሚደረገው ጦርነት የመከላከያው አጋር በመሆን ሲታገሉ የነበሩ ታጣቂዎች አንድ እዝ ስር እንዲጠቃለሉ የሚያደርግ አዲስ አዋጅ የወጣ ሲሆን ይህንን የሚያስተባብር አንድ ቢሮም ማቋቋማቸው ተዘግቧል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በካርቱም የጄኔራሉ ወታደሮች የጅምላ ግድያና እስር እየፈፀሙ መሆኑን የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ገልፀዋል፡፡ ከወራት በፊት ዋና ከተማዋን ካርቱምን የሱዳን ጦር ሀይል ከተቀናቃኙ ፈጥኖ ደራሽ ሀይል መንጠቁ ይታወሳል፡፡

የጦር ሀይሉ በከተማው ውስጥ እያካሄደ ባለው ዘመቻ ከፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ጋር ግንኙነት ነበራቸው ባላቸው ግለሰቦች ላይ የጭካኔ የብቀላ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የሱዳን የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ባሰራጩት መረጃ አስታውቀዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates