መካከለኛ ምስራቅ

ሐማስ በቀረበለት የጋዛ የተኩስ አቁም ላይ መስማማቱን ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 13/12/2017፡- ሐማስ ከእስራኤል ጋር በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ እና ታጋቾችን ለመልቀቅ በአሸማጋዮቹ የቀረበው ምክረ ሃሳብ ላይ መስማማቱን ቢቢሲ ዘግቧል።

ግብፅ እና ኳታር ያቀረቡት ምክረ ሃሳብ የአሜሪካ ልዑክ ስቲቭ ዊትኮፍ በሰኔ ወር ባቀረቡት ማዕቀፍ ላይ የተመሰረተ ነው ተብሏል።

በመጀመርያው 60 የተኩስ አቁም ቀናት ሐማስ ከቀሩት 50 እስራኤላውያን ታጋቾች መካከል ግማሹን፣ በሁለት ቡድን በመክፈል የሚለቅ ይሆናል።

በዚሁ ወቅት ቋሚ የተኩስ አቁም ላይ ድርድር ይኖራል ተብሏል።

የጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት ባለፈው ሳምንት ስምምነቱን ሊቀበል የሚችለው “ታጋቾቹ በሙሉ በአንድ ጊዜ የሚለቀቁ ከሆነ ብቻ ነው” ማለቱን ተከትሎ ምላሹ ምን ሊሆን እንደሚችል እስካሁን አልተገለፀም።

እሁድ ምሽት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ቴልአቪቭ አደባባይ በመውጣት መንግሥታቸው ጦርነቱን አሁኑኑ እንዲያቆም እና ሁሉንም ታጋቾች ለማስለቀቅ ከሐማስ ጋር ስምምነት እንዲደረግ መጠየቃቸው ይታወሳል።

የታጋቾች ቤተሰቦች በጋዛ ከተማ ሌላ ጥቃት መፈጸም በቁጥጥር ስር የሚገኙት እስራኤላውያንን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል የሚል ስጋት አላቸው።

ኔታንያሁ ሠልፈኞቹን የሐማስን የመደራደር አቋም አጠናክረውታል ሲሉ ከስሰዋል።

ፍልስጤማውያንም ሰኞ ዕለት በጋዛ ከተማ ባደረጉት የተቃውሞ ሠልፍ ጦርነቱ በአስቸኳይ እንዲቆም ጠይቀዋል።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ “የቀሩት ታጋቾች ሲመለሱ የምናየው ሐማስ ጫና ሲደረግበት እና ሲጠፋ ብቻ ነው!!! ይህ በፍጥነት በሚከናወንበት ጊዜ ስኬታማ የምንሆንበት ዕድል ይሰፋል” ሲሉ ጽፈዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates