አፍሪካ

በሊቢያ የሚገኙ ሱዳናውያን ስደተኞች የሊብያ ሱዳን ድንበር እንዲከፈትላቸው ጠየቁ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 12/12/2017፡- በሊቢያ የሚገኙ በርካታ ሱዳናውያን ስደተኞች በሊቢያ ያለውን አስቸጋሪ ሁኔታ ተከትሎ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ለማድረግ በሊቢያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ድንበር እንዲከፍቱ ባለሥልጣናቱን ጠይቀዋል።

ሊብያ፣ ግብፅና ሱደን የሚያገናኘውን የሶስት ማዕዘዠዝኑ ድንበር የፈጣን ድጋፍ ሰጭ ሃይሎች ከተቆጣጠሩት በኋላ ድንበሩ መዘጋቱ  የሚጠቅሙት መረጃዎቹ፤ ስደተኞቹ ወደ አገራቸው የሚመለሱበት ሌላ አማራጭ ጠባብ መሆኑ ገልጿል።

በቻድ በኩል ወደ ሱዳን ለመጓዝ ከፍተኛ ወጪ እንደሚጠይቃቸው የሚገልፁት ስደተኞቹ: በግብፅ በኩል ደግሞ ተራራዎችን በሚያቋርጡበት መንገድ ላይ የመታሰር እና የመሞት አደጋ እንደሚያጋጥማቸዘው ጠቁመዋል።

ስለሆነም ስደተኞቹ የሱዳን መንግስት እና የፈጣን ደጋፊ ሃይሎች መንገድን ከፍተው ቀጠናወ ከወታደራዊ እንቀስቃሴ ነፃ እንዲሆን እና በሺዎች የሚቆጠሩ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጠይቀዋል።

በምስራቃዊ ሊቢያ ቤንጋዚ የሚገኘው የሱዳን ቆንስላ በበኩሉ በሀገሪቱ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መሄዱን ተከትሎ ወደ አገራቸው መመለስ የሚፈልጉ ሱዳናውያን ምዝገባ መጀመሩን አስታውቋል።
ቆንስላ ጽ/ቤቱ ከመስከረም 25 በፊት የምዝገባ ሂደቱን ማጠናቀቅ እንደሚያስፈልግ አስታውቋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates