መካከለኛ ምስራቅ

በእስራኤል ህዝባዊ የተቃውሞ ተነሳ።

ተቃውሞው እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነት እንድትፈፅምና ተጋቾችን እንድታስለቅቅ የሚጠይቅ ነው።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 12/12/2017፡- በመቶ ሺ የሚቆጠሩ እስራኤላውያ የጋዛ ጦርነት እንዲያበቃና ታጋቾች እንዲለቀቁ የሚጠይቅ ሰፊ ህዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ በቴልአቪቭ አደባባይ አካሄዱ።

ከጥቅምት 2023 ወዲህ በእስራኤል ከተደረጉ ትላልቅ ሰልፎች መካከል አንዱ ነው በተባለው በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ የእስራኤል ጦር በጋዛ እያካሄደ ያለውን ጦርነት እንዲያቆም ብሎም በሃማስ ታግተው የሚገኙ እስራኤላውያን እንዲለቀቁ ከስምምነት እንዲደረስ ጥሪ ቀርቧል።

ሰልፉ የተዘጋጀው በታጋቾች እና በጠፉ ቤተሰቦች ፎረም በጋራ ሲሆን፣ የእስራኤል ጦር በጋዛ ከተማ የሚያደርገው ጥቃት የቀሩትን ታጋቾች ህይወት አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ገልጸዋል።

ይህ የተቃውሞ ማዕበል ከሳምንት በፊት የእስራኤል መንግስት ጋዛን ለመቆጣጠር ያጸደቀውን አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ በመቃወም የተካሄደ ሲሆን፤ መንግስት የወሰነው እርምጃ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ከማገዝ ይልቅ ህይወታቸውን አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል የሚል ስጋት እንዳላቸው ሰልፈኞቹ ገልጸዋል።

በቴል አቪቭ በሚገኘው “የታጋቾች አደባባይ” የተሰበሰበው ሰፊ ሕዝብ በርካታ መፈክሮችን በማሰማት ጦርነቱ እንዲያበቃ ጠይቀዋል።

“ሁሉንም ወደ ቤታቸው መልሱ! ጦርነቱን አቁሙ!” የሚሉት በስፋት በሰልፈኞቹ የተሰሙ የተቃውሞ ድምጾች ናቸው። “የእስራኤል መንግስት ፍትሃዊወእን ጦርነትን ወደ ትርጉም የለሽ ጦርነት ለውጦታል” ሲሉም ሰልፈኞቹ መንግስትን ተችተዋል።

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የተቃውሞ ሰልፉን በመተቸት “ሰልፉ የሃማስን አቋም እንደሚያጠነለናክር እና የታጋቾችን የመለቀቅ ሂደት እንደሚያዘገየው” ተናግረዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates