አፍሪካ

አቶ ጌታቸው ረዳ የኤርትራ ተቃዋሚው ድርጅት ብርጌድ ንሐመዱ ማነጋገራቸው ተሰማ።

የጠቅላይ ሚኒስትሪ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚገኙ ታውቋል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 08/12/2017፡ በኤርትራ ፍትህና ነፃነትን ለማረጋገጥ በውጭ አገር ሆኖ የሚታገለው ብርጌድ ንሓመዱ የተሰኘው አደረጃጀት አመራር የሆነው በየነ ገብረግዚአብሔር በ X ገፅ ባሰራጨው ፅሑፍ ከአቶ ጌታቸው ረዳ በዋሽንግተን ዲሲ ተገናኝተን  “በዲፕሎማሲያዊ ትስስራችን ውስጥ ያለውን እድገት ተወያይተናል” ብለዋል።

በተጨማሪም “ስለ እቅዶቻችን እና በአፍሪካ ቀንድ ላይ ስላለው ተጽእኖ ጥልቅ ውይይት አድርገናል” ብሏል።

የኤርትራ ዴሞክራሲ ለአፍሪካ ቀንድ እና ለመላው ዓለም ዘላቂ ሰላም ያመጣል ሲልም አቶ በየነ ተናግሯል።

ለበርካታ ዓመታት በውጭ አገር ሆኖ ሲታገል የቆየውን ብርጌድ ንሓመዱ በቅርብ ጊዝያት በአዲስ አበባ ፅ/ቤት መክፈቱ ይታወሳል።

በኢትዮጵያ መንግስት የስልጠና ቦታ እንደተሰጠው አስታውቆ የነበረው ድርጅቱ የኤርትራ ስርዓትን በትጥቅ ትግል ለማስወገድ መወሰኑ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ከብርጌድ ንሓመዱ በተጨማሪ የኤርትራ ቀይ ባህር ዓፋር ህዝቦች ግንባርም እንደሚደግፍ  ይነገራል።

በዚህም አርሳዶ በሚል የሚታወቀዉ  የኤርትራ ቀይ ባህር ህዝቦች ግንባር በዓፋር ክልል ሰመራ ከተማ ፅ/ቤት መክፈቱ አስታውቋል።

አርሳዶ የኤርትራ መንግስትን ለማስወገድ የትጥቅ ትግል እንደሚጀምር ያስታወቀ ሲሆን ከአቶ ጌታቸው ረዳ በሰመራ ውይይት ማድረጉ ይታወሳል።

በሌላ በኩል የኤርትራ መንግስትም ከዓፋር ክልል ወደ ኤርትራ የገቡ ታጣቂዎችና ሌሎች በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ቡድኖች ደሰጋፍ እንደሚሰጥ ይታወቃል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates