
ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/12/2017፡ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከአዘርባጃን እና ከአርሜኒያ መሪዎች ጋር በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፣ የሶማሊላንድን ዓለም አቀፍ ዕውቅና የማግኘት የረጅም ጊዜ ጥያቄን በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
ትራምፕ ስለ ሶማሊላንድ ጥያቄ ተጠይቀው ሲመልሱ፣ “ጥሩ ጥያቄ ነው፣ አሁን እየተመለከትነው ነው” ብለዋል፣ ይህም ዩናይትድ ስቴትስ ጉዳዩን በንቃት እያጤነችው መሆኑን ያመለክታል ሲል ሆርን ትሪቢውን ዘግቧል።
ሶማሊላንድ እ.አ.አ ከ1991 ከሶማሊያ ነፃነቷን ካወጀችበት ጊዜ አንስቶ፣ ከሶማሊያ ጋር ሲነፃፀር በተሻለ መረጋጋት እና ዴሞክራሲያዊ አስተዳደር ቢኖራትም፣ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ መደበኛ ዕውቅና ሳታገኝ ቆይታለች።
የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት አብዲራህማን መሐመድ አብዱላሂ እ.አ.አ በ2025 የዓለም መንግስታት ጉባኤ ላይ እንደተናገሩት፣ እውቅና ማግኘታችን “ቅርብ ነው” ብለው ተስፋቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ለዚህ አሜሪካ ቀዳሚ ልትሆን እንደምትችል ገልጸው ነበር።