መካከለኛ ምስራቅ

እስራኤል በጋዛ በፈፀመችው ጥቃት አምስት የአልጀዚራ ጋዜጠኞች መገደላቸው ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/12/2017፡ በጋዛ ከተማ አልሺፋ ሆስፒታል አቅራቢያ እስራኤል ባደረሰችው ጥቃት አምስት የአልጀዚራ ጋዜጠኞች መገደላቸውን ተቋሙ ገልጿል።

ዘጋቢዎቹ አናስ አል ሻሪፍ እና መሀመድ ቂቀህ ከካሜራማን ኢብራሂም ዛህር፣ መሀመድ ኑፋል እና ሞአመን አሊዋ ጋር በሆስፒታሉ ዋና በር ላይ በሚገኝ ድንኳን ውስጥ ነበሩ ሲል አልጀዚራ ዘግቧል።

ኣልጄዚራ “በፕሬስ ነፃነት ላይ ግልጽ እና ሆን ተብሎ የተደረገ ጥቃት ነው” ሲል በመግለጫው ገልጿል።

ከጥቃቱ በኋላ ብዙም ሳይቆይ የእስራኤል መከላከያ ሃይሉ አናስ አል ሻሪፍ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መሆኑን አረጋግጦ በቴሌግራም ፖስት ላይ ባጋራው መረጃ ጋዜጠኛው “በሃማስ የአሸባሪ ቡድን መሪ ሆኖ አገልግሏል” ሲል ጽፏል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates