አፍሪካ
በማቀዝቀዣ መኪና ውስጥ ተደብቀው እንግሊዝ ለመግባት የሞከሩ 15 ኤርትራዊያን ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መግባቱ ተገለፀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 05/12/2017፡ መኪናው ቀዝቃዛ አትክልቶችን ጭኖ ከሰሜናዊ ፈረንሳይ ተነስቶ ወደ እንግሊዝ እየተጓዘ እንደነበር ተገልጿል፡፡
በጉዞው መሀል ላይ ግን የሰዎችን ጩኾት በመስማቱንና መኪናውን ለማቆም መገደዱን መረጃው ያሳያል፡፡
ከዚያም የመኪናው ማቀዝቀዣ ጭነት ሲከፈት 15ቱ ኤርትራዊያን ሊገኙ መቻላቸውን ኤኤፍፒ ዘግቧል፡፡
ስደተኞቹ ሰውነታቸው ከመጠን በላይ ቀዝቅዞ እንደነበርና ይህም ለሰአታት በመኪና ውስጥ መቆየታቸውን የሚያሳይ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከእነዚህ መካከል 4ቱ ለከፍተኛ የጤና ችግር በመዳረጋቸው ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የጠቀሰው ዘገባው በውስጡ ከነበሩት መካከል 4ቱ ህፃናት መሆናቸውንም አስረድቷል፡፡
የከተማው ፖሊስ እንደገለፀው ከእነዚህ ኤርትራዊያን መካከል አብዛኛዎቹ ፈረንሳይን ለቀው እንዲወጡ የታዘዙ ናቸው፡፡