የኮሎምቢያ ፕሬዝዳንት ሱዳን ውስጥ ህጻናትን ወታደር እያሰለጠኑ ነው በተባሉት ቅጥረኞች ላይ እርምጃ እንደሚወስዱ ቃል ገቡ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 02/12/2017፡ በሱዳን ጦርነት ውስጥ የቅጥረኞች ተሳትፎ እያደጉ መሄዳቸው የኮሎምቢያው ፕሬዝዳንት ጉስታቮ ፔትሮ በዳርፉር የህጻናት ወታደሮችን እያሰለጠኑ ነው በተባሉት “ኮሎምቢያዊያን” ላይ እርምጃ እንዲወስዱ አነሳስቷቸዋል።
የሱዳን ጦር በዚህ ሳምንት ከሰራዊቱ ጋር ባደረገው የሁለት አመት ጦርነት በሲቪል ጭፍጨፋ እና ሌሎች ጭካኔዎች የተከሰሰውን በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሃይል ቡድን ውስጥ ያሉትን የውጪ ቅጥረኞች የሚያሳይ ቪዲዮዎችን መልቀቁ ይታወሳል።
በምዕራብ ሱዳን ኤል ፋሸር የምትባል የዳርፉር ከተማን ለረጅም ጊዜ ከቧት ከሚገኘው ታጣቂ ቢድኑ ጋር ከተቀላቀሉት 80 የሚገመቱ የኮሎምቢያ ቅጥረኞች እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።
ሠራዊቱ በከተማው ውስጥ የRSF አዛዥ ሆኖ ሲያገለግል የነበረውን ጨምሮ በርካታ ኮሎምቢያውያንን ገድያለሁ ብሏል።
እንዲሁም ቅጥረኞች ጭና በኒያላ አየር ማረፊያ እየደረሰች በነበረችው የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ አውሮፕላን ባደረስኩት ጥቃት 40 የኮሎምቢያ ቅጥረኞች ገድያለሁ ማለቱ ይታወሳል።
ፕሬዝዳንት ፔትሮ በአስቸኳይ ምርመራ እንዲካሄድ ትዕዛዝ የሰጡ ሲሆኒ በአስቸኳይ ቅጥረኞችን የሚከለክል ህግ እንዲፀድቅም ትእዛዝ አስተላልፏል።
የኮሎምቢያው መሪ እሮብ ምሽት ላይ በማህበራዊ ሚድያ ባጋሩት ፅሑፍ ላይ ቅጥረኞቹ “የሞት ተመልካቾች ናቸው” ብለዋል።
ጨምሮም “ወጣት ወንዶችን በከንቱ እንዲገድሉ እና እንዲገደሉ የሚልኩ አለቆች ነፍሰ ገዳዮች ናቸው” ብሏል። “እንዲሁም ሰዎችን ለመግደል ወደ ሸቀጥነት የሚቀይር የሰዎች ዝውውር አይነት ነው” ብሎታል ተግባሩን።
የ40 ሰዎች ሞት ሪፖርት ያልተረጋገጠ ነው ያሉት ፕሬዝዳንት ፔትሮ በግብፅ የሚገኘውን የኮሎምቢያ ኤምባሲ የሟቾችን ቁጥር እንዲያጣራ እና የማንኛውም ኮሎምቢያውያን አስከሬን ወደ ትውልድ አገራቸው መመለስ ይቻል እንደሆነ ለማየት መጠየቃቸው ተዘግቧል።
በኒያላ አቅራቢያ በሚገኙ የRSF ካምፖች ውስጥ የሚገኙ የኮሎምቢያ ቅጥረኞች ወታደራዊ ስልጠናዎችን እየሰጡ ሲሆን ከእነዚህም መካከል አንዳንዶቹ እስከ 10 አመት እድሜ ያላቸው ህጻናትን ጨምሮ በዚህ ሳምንት በኮሎምቢያ የዜና ጣቢያ ላሲላ ቫቺያ ባወጣው የምርመራ ዘገባ ተረጋግጧል።