አፍሪካኢትዮጵያ

የኢትዮጵያ መንግስት ሊወረኝ በሱዳን በኩል እየመጣብኝ ነው ሲል የኤርትራ መንግስት ክስ አቀረበ።

በአፋር በኩሉም ተመሳሳይ እንቅስቃሴዎች እንዳሉ ደርሼበታለሁ ብሏል።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 28/11/2017፡ የኢትዮጵያ መንግስት በሱዳንና ሑመራ በኩል የጦር መሳሪያ እያንቀሳቀሰ እንደሆነም ሻዕቢያ በልሳናቱ በኩል እያስተጋባ ነው።

የብልፅግና ስርዓተ ኢትዮጵያ ውስጥ ካለው አለመረጋጋት ማምለጫና አጀንዳ መቀየሪያ ወደማይሆን አደጋ እየገባ ነው የሚሉት የሻዕቢያ ሚድያዎች ይህም በኤርትራና ሱዳን ድንበር በሁመራ በኩል እየተመለከትን ነው ብሏል።

“በምስራቅ ሱዳን ጦርነት ከፍቶ ቢያንስ በተቀናቃኙ የሱዳን መንግስት ወታደሮች ላይ የስነ ልቦና ጫና ለማሳደር የታጠቁ ተሽከርካሪዎችን በሁመራ በኩል ወደ ኤርትራ ድንበር እየዘመተ ነው” ሲል ከሷል።

የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራና በኢትዮጵያ ምዕራባዊ ድንበሮች ላይ የሚሊተሪ ኮንሴንትሬሽን ፎር ታክቲካል ዳይቨርጀንስ የሚባለውን የምዕራባዊያን አባባል የጦርነት ስትራቴጂ እያሰበ ነው የሚለው መረጃው ይህም ዞሮ ዞሮ የኤርትራን ጦር የበለጠ ለመምጠጥ እና ለማዘናጋት ያለመ ነው ብሏል።

“በአንድ ምሽግ ውስጥ ተቀምጦ ተራውን የፋኖ ታጣቂ ቡድን መታገል የማይችል ሰራዊት” በማለት የኢትዮጵያ ሰራዊትን የገለፀው ሻዕቢያ ከፕሮፓጋንዳ የዘለለ ሌላ “ተአምር” እርምጃ ሊወስድ እንደሚችል መገመት ከባድ አይደለም ብሏል።

የብልፅግና አገዛዝ ለሱዳን ጦር አዛዥ ሌተናል ጀነራል አብዱልፈታህ አል ቡርሃን በልዑካኑ በኩል ያቀረበው “ደፋር” ጥያቄ በማለት ሁለት ነጥቦችን የጠቀሱት የሻዕቢያ ሚድያዎች “ኤርትራን ስንወጋ እንድትደግፈን አንጠይቅም ነገር ግን ገለልተኛ ሁኑ” የሚለው አንደኛ ነጥብ መሆኑ ጠቅሷል።  ሁለተኛው የትግራይ “አርሚ 70” እየተባለ የሚጠራው እና ከናንተ ጋር የሚዋጋውን “አሳልፈህ ስጠኝ” የሚል መሆኑ ጠቅሷል። ይህ ግን እንደማይሆን በአልቡርሃን በኩል ምላሽ እንደተሰጠ ገልጿል።

አስፈላጊ ከሆነም ሳዋ ውስጥ የሰለጠኑ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ሊቀላቀሉበት ይችላሉ የሚለው ሻዕቢያ ብልፅግና  በደቡባዊ ሱዳን ኮርዶፋን ግዛት የሚገኘውን የፈጣን ድጋፉ  ሰጪ ሐይሎች ወታደሮች በምዕራብ በኩል ጦርነት በመክፈት “የሶስትዮሽ ጦርነት” እንዲጀመር እየሰራ እንደሆነ ይከሳል።

በምስራቃዊ አፋር በኩልም ተመሳሳይ እንቅስቃሴ እንዳለ እየተከታተልኩት የቆየሁት ነገር ነው የሚለው ሻዕቢያ ይህም የኢትዮጵያ መንግስት በውስጡ እያጋጠመው ያለውን ፖለቲካዊ ቀውስ ለማምለጥ የሚያደርገው ሩጫ እንደሆነ ገልጿል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates