አፍሪካ

በሱዳን ኮርዶፋን ግጭት እየተባባሰ በመምጣቱ መፈናቀል እና ሞትን እየጨመረ መምጣቱ ተገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 25/11/2017፡ በሱዳን ኮርዶፋን ግዛት በሶስቱ ግዛቶች የተቀሰቀሰው ጦርነት በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት፣ የጅምላ መፈናቀል እና ለመሠረታዊ አገልግሎቶችን መቋረጥ ምክንያት መሆኑን አለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታወቋል።

ኮሚቴው በመግለጫው “በሱዳን ኮርዶፋን ግዛቶች በሲቪሎች እና በአስፈላጊ መሰረተ ልማቶች ላይ በተፈጸሙ ጥቃቶች ሆስፒታሎች፣ ገበያዎች እና የመኖሪያ አካባቢዎች ከፍተኛ መጠን ያላቸውን ጉዳቶች አስከትለዋል፣ የጅምላ መፈናቀል እና አስፈላጊ አገልግሎቶች ወድመዋል ይላል ሚድል ኢስት ሞኒተር ያወጣው መረጃ።

በሱዳን የሚገኘው አለም አቀፉ የቀይ መስቀል የልዑካን ቡድን መሪ ዳንኤል ኦማሌይ በመግለጫው “እ.ኤ.አ. ከ 2025 መጀመሪያ ጀምሮ በኮርዶፋን ግዛቶች የሚካሄደው ውጊያ ተጠናክሮ በመቀጠሉ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት እና የሀገሪቱን ሰብዓዊ ቀውስ አባብሷል። በአንዳንድ አካባቢዎች 90 በመቶው ሰላማዊ ዜጎች ተሰደዋል” ብሏል።

ከጦርነቱ ጎን ለጎን ያልፈነዱ የጦርነት ቅሪቶች በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተለይም የግጭት ቀጠናዎችን ለቀው ለሚሰደዱ ወይም ወደ ቤታቸው ለመመለስ በሚሞክሩት ላይ ከፍተኛ ስጋት እንደሚፈጥሩም አክለዋል።
ሶስት ዓመታትን ሊሞላው ወራቶች የቀረው የሱዳን እርስ በርስ ጦርነት የውጭ ሐይሎች እጅ እንዳለበት ይገለፃል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates