ኢትዮጵያፖለቲካ

ስምረት ፓርቲ በመቀሌ ከተማ የሚገኘው ጽህፈት ቤቱ በታጣቂዎች መፍረሱ ገለፀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 23/11/2017፡ “በፓርቲው ዋና ፅህፈት ቤት የሚፈፀመውን ህገወጥ ድርጊት ሁሉም ሊያወግዘው ይገባል” ሲል ፓርቲው በፌስቡክ ገጹ በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ሀምሌ 22 ቀን 2017 ከምሽቱ 4፡45 ላይ ማንነታቸው ያልታወቁ ማስክ የለበሱ ታጣቂዎች በመቀሌ ከተማ በሚገኘው የዲሞክራሲያዊ ስምረት ፓርቲ ዋና ፅህፈት ቤት ጥቃት መሰንዘራቸውን ፓርቲው አስታውቋል።

“በአስገድዶ ዛቻና የሕንፃውን ነደኅንነት ጥበቃ በመግፋት ዋና መሥሪያ ቤታችን ላይ የተለጠፈውን ባነር መቅደዳቸውን አረጋግጠናል” ሲል ስምረት በመግለጫው ተናግሯል።


ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 10 ቀን 2017 ዓ.ም (አ1262/11/15569) ለትግራይ ክልላዊ መንግስት ይፋዊ ደብዳቤ መላኩ ይታወሳል። ደብዳቤው ስምረት ፓርቲ በመላው ትግራይ ተንቀስቅሶ የአባላት ምዝገባ እንድያደርግ በጊዝያዊ አስተዳደሩ ትብብር እንዲደረግለት የሚጠንቅ ነው።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በፓርቲው ጽ/ቤት ላይ የተፈፀመውን ህገወጥ ተግባር አጣርቶ ህግ እንዲያከብር እንጠይቃለን ሲል ስምረት ፓርቲ አስገንዝቧል።

ፓርቲው ሐምሌ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በመቀሌ ከተማ ሊያካሂደው የነበረው  የጽህፈት ቤቱን የመክፈቻ ፕርግራም ባልታወቀ ምክንያት መሰረዙ ይታወሳል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates