አፍሪካ

የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ የኤርትራን መንግሥት በትጥቅ ለመታገል በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ

ኢትዮ ሞኒተር፡ 23/11/2017፡ የኤርትራን መንግሥት ለመጣል ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች አንዱ እንደሆነ የገለፀው “የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ” ኢትዮጵያ ውስጥ ሆኖ የትጥቅ ትግል ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታወቀ።

የኤርትራ አፋር ብሔራዊ ጉባኤ የሥራ አስፈጻሚ አባል እና ቃል ዐቀባይ አሊ መሐመድ ዑመር፤ “የኢትዮጵያ መንግሥት የመንቀሳቀስ እና የመናገር ዕድል ሰጥቶናል” ሲሉ ገልጸው፤ አፋር ክልል ሰመራ ከተማ ውስጥ ጽ/ቤት መክፈታቸውንና አዲስ አበባ ላይም ለመክፈት በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ ለዶቼ ቬለ ገልፀዋል።

ቃል ዐቀባዩ፤ ባለፈው ሳምንት በዋናነት በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ እና ጅቡቲ የሚገኙ አፋሮችን በሚመለከት እና በአካባቢው ቀጣናዊ ኹኔታዎች ዙሪያ ጠለቅ ያለ ውይይት በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ መደረጉንና ድርጅታቸውም መሳተፉን ገልፀዋል።

“የኤርትራ አፈር ብሔራዊ ጉባኤ” ከ11 ዓመታት በፊት እ.አ.አ በ 2014 ስዊድን ውስጥ ተመሥርቶ ለዓለም አቀፍ ተቋማትና ሀገራት ኤርትራ ውስጥ ስላለው “ፈታኝ” ያሉት ኹኔታ ሲያስገነዝብ፣ ሲሰባሰቡም መቆቱን የገለፁት አሊ መሐመድ ፤ አሁን ወደዚህ የመጡበት ምክንያት ምን እንደሆነም አስረድተዋል።

የኢትዮ ኤርትራ ውጥረት፤ ከቋፍ ላይ መድረሱ መረጄዎች እየወጡ ናቸው፡፡ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ በአንደበታቸው ከኢትዮጵያ ጋር መዋጋት አንፈልግም ቢሉም በድርጊታቸው ግን አደገኛ እንቅስቃሴን እያደረጉ እንደሆነ ነው የሚወጡ መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡

ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኤርትራ ጦር እና ከባድ መሳሪያ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እየተጠጋ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ሻዕብያን ከስልጣን ለማስወገድ የሚንቀሳቀሰው የኤርትራ አፈር ብሔራዊ ጉባኤ ስለ ኤርትራ ጦር አደገኛ እንቅስቃሴ አዲስ መረጃን አጋርቷል፡፡

ጉባኤው፣ ኤርትራ የጦር ሠራዊቷን ወደ ኢትዮጵያ ድንበር እያስጠጋች ነው ብሏል፡፡ የጉባኤው የሥራ አስፈጻሚ አባል እና ቃል ዐቀባይ አሊ መሐመድ ዑመር ለጀርመን ድምጽ በሰጡት ቃል፣ ‹‹የኤርትራ መንግስት ድንበር ላይ ኃይለኛ እንቅስቃሴዎች በከባድ መሣሪያ የታገዘ ሠራዊት አቅርቧል፤ ቡሬ አካባቢ። ስለዚህ አሁንም ወደ ጦርነት የመግባት እና ኢትዮጵያን ሰላም የመንሳት ፍላጎቱ እንደቀጠለ ነው›› ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ግንኙነት ከፕሪቶሪያው ዘላቂ የግጭት ማቆም ምምነት ወዲህ እና በተለይ ኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት የሕልውናዋ ጉዳይ መሆኑን ለዓለም ማሳወቋን ተከትሎ ፍጥጫ ውስጥ ገብተዋል፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates