ማህበራዊ

የጦር መሣሪያዎች እንዳገኘ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 22/11/2017፡ በአዲስ አበባ በአልጋ ቤቶች ላይ በተደረገ ድንገተኛ ፍተሻ አራት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ከ298 ጥይቶች ጋር መያዙን ፖሊስ አስታውቋል።

የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በአዲስ አበባ ከተማ ወረዳ ሰባት ልዩ ቦታው 32 ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙ አልጋ ቤቶች ላይ “በተደረገ ፍተሻ”፣ “አራት ክላሽንኮቭ መሳሪያ ከ298 ጥይቶች” ጋር መያዙን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ፤  “የመዲናዋን ሠላምና ፀጥታ አስተማማኝ ለማድረግና አጠራጣሪ ጉዳዮች ባጋጠሙበት ወቅት ጭምር ድንገተኛ እና የተጠና ፍተሻና አሰሳ እንደሚደረግ” ገልጸዋል።

የጦር መሳሪያዎቹ “መኝታ ቤቶችን በሚያከራዩ ቤቶች ውስጥ የተያዙ” ሲሆን፣ እነዚህ ቤቶች “ከፍተኛ የሰዎች እንቅስቃሴ ያለባቸው  እና ውስን ቁጥጥር የሚደረግባቸው መሆናቸውን” የከተማዋ ፖሊስ አመልክቷል።

ፖሊስ የወንጀል ድርጊቱ ተሳታፊ ነበሩ ያላቸው ፍቃዱ ማናየ፣ አዳነች ጎበዜ፣ ዮሀንስ ፍቃዱ እና ዮናስ በቀለ የተባሉ ግለሰቦች ላይ ተገቢው ምርመራ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን በማሰባሰብ በህግ አግባብ ለማስጠየቅ እንደሚሰራ ኮማንደር ማርቆስ ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ መግብያና መውጭያዎችን ጨምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ድንገተኛ ፍተሻዎች እንደሚያደርግ  የፌደራል ፖሊስ ባለፈው ሳምንት ማስታወቁ ይታወሳል። ማህበራዊ ሚድያን ተጠቅሞ የአገሪቱን ሰላምና መረጋጋትን የሚረብሹ ላይም እርምጃ እንደሚወስድ መግለፁ አይዘነጋም። ይህን ተከትሎ በርካቶች ድርጊቱን የዜጎች ሐሳብን የመግለፅ መብት የሚገድብና ሽብርን የሚፈጥር ተግባር ነው ሲሉ ሲቃወሙት ነበር።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates