ኢትዮጵያፖለቲካ

ለአንድ ሳምንት ተዘግቶ የቆየውን የደቡብ ትግራይ ዞን አስተዳደር ስራ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 22/11/2017፡ የዞኑን አስተዳደር አመራሮች የመቀየር ስራ መጀመሩን የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝደንት ሌተና ጄኔራል ታደሰ ወረደ ማስታወቃቸውን ተከትሎ በዞኑ ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ መነሳቱ ይታወቃል፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ፕሬዝደንቱ ከዞኑ ህዝብና አመራሮች ጋር ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡ በውይይቱም የዞኑን አስተዳዳሪ ሀፍቱ ኪሮስን ጨምሮ የነበሩት አመራሮች በሙሉ ወደስልጣናቸው እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ እንዲሁም የአመራር ለውጡን ተግባራዊ ለማድረግ በሚል የተቋቋመው ‹‹ኮማንድ ፖስት›› እንዲፈርስ መስማማታቸው ተሰምቷል፡፡

በተጨማሪም ያለውን የፖለቲካ ልዩነት በተመለከተ ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት የሚሳተፉበት ሰላማዊ ውይይት ለማድረግ የዞኑ ካቢኔ የተስማማ ሲሆን ይህንን ተከትሎ የዞኑ አስተዳደር መስሪያ ቤቶች በሙሉ ተከፍተዋል፡፡

የዞኑ አስተዳደር ባወጣው መግለጫም ‹‹ለ6 ቀናት ያህል ተዘግተው የነበሩት የአስተዳደር ቢሮዎች በሙሉ ተከፍተዋል፡፡ አቶ ሀፍቱ ኪሮስም በቢሯቸው ስራቸውን እያከናወኑ ነው›› ብሏል፡፡
ጊዝያዊ አስተዳደሩና የዞኑ ካቢኔ ለተጨማሪ ወይይት ለሐምሌ 27 ቀጠሮ ይዟል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates