አፍሪካ
በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ሐይል የሚመራ ጥምር መንግስት በጦርነት በምትታመሰው ሱዳን ውስጥ ትይዩ መንግስት መመስረቱ ታወቀ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 21/11/2017፡ ጥቃት እና የመብት ረገጣ እየተባባሰ በመጣበት በዚህ ወቅት ጥምረቱ ‘ሴኩላር፣ ዲሞክራሲያዊ’ እና ያልተማከለ አስተዳደርን ሱዳን ውስጥ ለመከተል ቃል ገብቷል።
በፈጣን የድጋፍ ሃይሎች የሚመራ የሱዳን ጥምር ጦር በዋና ከተማይቱ ካርቱም ወታደራዊ-የሚመሩ ባለስልጣናትን በመቃወም ተለዋጭ መንግስት በማቋቋም ላይ መሆኑን አስታወቋል።
ራሱን የሱዳን መስራች ህብረት አመራር ምክር ቤት ብሎ የሚጠራው ቡድን የ RSF መሪ መሀመድ ሃምዳን ዳጋሎ የክልል ገዢዎችን ያካተተ 15 አባላት ያሉት የመንግስት ፕሬዝዳንታዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ይሆናሉ ተብሏል።
የሱዳኑ ፖለቲከኛ መሐመድ ሀሰን ኦስማን አል-ታኢሺ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ያገለግላሉ ብለዋል ሕብረቱ።
“በዚህ ታሪካዊ ስኬት ላይ የአመራር ምክር ቤቱ ሰላምታና ደስታን ለአስርት አመታት አውዳሚ ጦርነቶችንላሳለፈው ለሱዳን ህዝብ ይድረሰው” ሲል ጥምረቱ በመግለጫው ገልጿል።
በሌላ በኩል በጄነራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን የተሾሙት ጠቅላይ ሚኒስትር ካሚል ኢድሪስ አምስት ሚኒስትሮችና ሶስት ሚኒስትር ዲኤታዎች መሾማቸው ተገልጿል።