ማህበራዊአፍሪካ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ ከምግብ ሥርዓት ጋር እንዲጣጣም ጥሪ አቀረቡ።

ኢትዮ ሞኒተር፡ 21/11/2017፡ በኢትዮጵያና በጣሊያን መንግሥት ትብብር የተዘጋጀው ሁለተኛው የተባበሩት መንግሥታት የምግብ ስርዓት ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መሰብሰቢያ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በጉባኤው ላይ መክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ የአየር ንብረት ለውጥ ፋይናንስ ከምግብ ሥርዓት ጋር እንዲጣጣም ለጉባዔው ተሳታፊዎች ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ለልማት የሚደረጉ ድጋፎች በመቀዛቀዛቸው ምክንያት አፍሪካ ጫና ውስጥ እንደምትገኝ እና የባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ፈተና እንደገጠማቸው የገለጹ ሲሆን፤ አህጉሪቱ በግብርና፣ የገጠር ልማት፣ መሠረተ ልማት እና ቢዝነስ ላይ ኢንቨስት እንድታደርግ ተገማች ፋይናንስ እንደሚያስፈልጋት ተናግረዋል፡፡

“ከእኛ አውድ ጋር የሚስማሙ ከአየር ንብረት ጋር የተዛመኑ መሳሪያዎች፣ ባዮቴክኖሎጂ እና የዲጂታል ግብርና ያስፈልጉናል። ቴክኖሎጂዎች ተመጣጣኝ እና የጋራ ሊሆኑ እንጂ ሊደበቁ አይገባም” ሲሉ አጽዕኖት ሰጥተዋል።


መንግሥት የምግብ ስርዓትን ለማጎልበት ከ700 በላይ የተግባር እርምጃዎችን በመውሰድ፤ በ7 ክላስተር ከፌዴራል እስከ ክልል ብሎም ተቋማትን ያሳተፉ ሥራዎች እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከፈረንጆቹ 2021 ጀምሮ የምግብ ስርዓት ፍኖተ ካርታ በማዘጋጀት ከሀገር በቀል የምጣኔ ሀብት ማሻሻያ ስርዓቱ ጋር በማጣጣም በተከናወኑ ተግባራት የተመዘገቡ ለውጦችን ያብራሩም ሲሆን፤ የምግብ ስርዓቱ አካታችና ዘላቂ እንዲሆን እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ቀጣይነት ያለው፣ አካታች እና የማይበገር የምግብ ስርዓት ግንባታ ላይ ትኩረቱን ያደረገው የመሪዎች ጉባኤው ከሐምሌ 20 እስከ 22 ድረስ የሚካሄድ ሲሆን፤ በዚህም ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽንን አስመልክቶ ያገኟቸውን ስኬቶችና ያጋጠሟቸው ተግዳሮቶች በተመለከተ ሪፖርት ያቀርባሉ።

በዚህም ጉባኤ ላይ ያልተገኙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በቪድዮ ለጉባኤው መልዕክት አስተላልፈዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates