
ኢትዮ ሞኒተር፡ 21/11/2017፡ ከኢትዮጵያ 12 ክልሎች እና ሁለት ከተማ መስተዳደሮች የተውጣጡ ከ50 በላይ የሚሆኑ የሀገር ሽማግሌዎች፣ አባ ገዳዎች እና ነጋዴዎች ዛሬ ሐምሌ 21 ቀን 2017 ዓ/ም ወደ ትግራይ ተጉዟል።
ከአሉላ አባ ነጋ አየር ማረፊያ ጀምሮ በትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር አቀባበል የተደረገላቸው የሰላም ልኡኳኑ “እኛ ስለተቀበላችሁን እናመሰግናለን” ያሉ ሲሆን፣ ጦርነቱን በመፍራት ልዩነቶቻቸውን በውይይት ለመፍታት መምጣታቸውን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ሰላም ትፈልጋለች ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ወደዚህ ከመምጣታችን በፊት ለ15 ቀናት ያህል ተወያይተናል ሲሉም አክለዋል።
” የጀመረው ሰላም እንዲፀና ፤ ዳግም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ከመስራትና ከመጣር የበለጠ ሃይማኖታዊና አባታዊ ተልእኮ የለንም ለዚህም የሚከፈለውን ሁሉም ዓይነት መስዋእትነት እንከፍላለን ” ብለዋል።
ልዑካኑ ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ፣ከህወሓት አመራሮች ፣ተፎካካሪ ፓርቲዎች እና ሲቪክ ማህበራት ጋር ተገናኝተው ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል። በነገው እለትም በተያዘላቸው መርሃ ግብር ተፈናቃዮቹን በአካል ይጎበኛሉ ተብሏል።
ለተፈናቃዮችም 30 ሚሊዮን ብር ይዞ መጓዛቸው ታውቋል። ከሁለት ሳምንታት በፊት ወደ መቐለ የተጓዙት የአገር ሽማግሌዎች የትግራይ ተፈናቃዮችን ሳይጎቦኙ መመለሳቸው ብዙ ትችት ሲቀርብባቸው እንደነበር ይታወሳል።