አፍሪካ

በሱዳን የሰብአዊ መብት ጥሰት ተባብሰዋል፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 11/11/2017፡ በሱዳን በሳምንቱ መጨረሻ በሰሜን ኮርዶፋን ግዛት በራ አካባቢ በደረሰ ጥቃት 35 ህጻናት እና ሁለት ነፍሰ ጡር ሴቶችን ጨምሮ ከ450 በላይ ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ተገለፀ።

በጥቃቱ ብዙ ሰዎች ቆስለዋል እንዲሁም ሞቷል፣ ዩኒሴፍ የተጎጂዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል የሚል ስጋት እንዳለው ገልጿል።

በአፍሪካ የአውሮፓ የውጭ ፕሮግራም ሪፖርት እንዳመለከተው ጥቃቱ በፈጣን የድጋፍ ሃይል  እንደተፈፀመ፣ እንደ እማኞቹ ገለጻ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ በጥይት መትቶ በእሳት አቃጥሏቸዋል።

በሰሜን ዳርፉር በኤል ፋሸር  ባገረሸው የታጣቂ ሐይሉ አዲስ የተኩስ ጥቃት 5 ህፃናት መሞታቸው ተዘግቧል።

ከአንድ ቀን በፊት በኒቫሻ ገበያ በሮኬት የሚንቀሳቀሱ የእጅ ቦምቦች ተጨማሪ 6 ሰዎች መገደላቸው ተገልፀዋል።
ይህ በእነሰዲህ እንዳለ በሱዳን የክትባት መጠን በከፍተኛ ደረጃ እያሽቆለቆለች መሆኗን የአለም ጤና ድርጅት ዘግቧል።


የሱዳን የህግ ባለሙያዎች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ባለፈው ሳምንት የአለም አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ያቀረበውን ሪፖርት ውጤታማ ያልሆነ እና ተጨባጭ ውጤት በለማምጣቱ አውግዘዋል።

ከዳርፉርም በላይ በሌሎች አከባቢዎች ሰፊ ምርመራ እንዲደረግም ጠይቀዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates