
ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ አርሳዶ ከቀይ ባህር አፋር ህዝብ ጋር በሰመራ ከተማ ባደረገው ውይይት የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ኢብራሂም ሀሮን የአስመራው ፋሽስታዊ መንግስትን ለመታገል ያቀደውን አዲሱን እቅድ እንዲሁም በወቅታዊው የፖለቲካ ሁኔታ ላይ ለህዝቡ ማብራርያ መስጠታቸው ታውቋል።
በአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መዲና ሰመራ-ሎጊያ በሚገኘው የማህበረሰብ ማዕከል በተካሄደው ዝግጅት ላይ የRSADO በየደረጃው የሚገኙ አመራር አካላትን ጨምሮ የቀይ ባህር አፋር ህዝብ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት ሲሆን ባህላዊ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ መሳተፋቸው ተገልጿል ።
ሊቀመንበሩ አቶ ኢብራሂም ለቀይ ባህር አፋር ህዝብ በክልሉ ስላለው የፖለቲካ ሁኔታ፣ በኤርትራ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና እና የRSADO በኤርትራ ለውጥ ለማምጣት ያለውን ቁርጠኝነት አስመልክቶ ማብራሪያ መስጠታቸው መረጃው አመልክቷል።
ኢብራሂም “በአስመራ ያለው ፋሺስታዊ መንግስት በቀይ ባህር አፋር ህዝብ ላይ በሰው ልጆች ላይ ወንጀል ቢፈጽምም የህዝቦች አንድነት፣ ፅናት እና የህይወት ተስፋ አምባገነኑን ስርዓቱን ለመታገል እና ወደ ትውልድ አገራቸው ለመመለስ ያላቸውን ፍላጎት ተስፋቸው አልቆረጠም” ብለዋል።
በክልሉ ባለፉት ሰባት አመታት በተከሰተው የጂኦ-ፖለቲካዊ ቀውስ ተለዋዋጭነት የተለያየ ሃይሎችን በማሰለፍ አመራሩ ነቅቶ በመጠበቅ የድርጅቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚጎዳ ስህተት እንዳይሰራ እንደሰራም ገልጿል።
አርሳዶ ‘’ራስን በራስ መወሰን እስከ መገንጠል’’ በሚል የፖለቲካ መፈክር ከአስመራ መንግስት ጋር የሚያደርገውን ትግል ለመደገፍ ለህዝቡ ጥሪ አቅርቧል።