
ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ በአለም ላይ ወቅታዊ ትኩረት የተሰጠው የ2025 የBRICS አባል አገራት ስብሰባ በብራዚል ሪዮ ዲጀኔሪዮ ከተማ ለሁለት ቀናት ተካሂደዋል፡፡
ባለፈው ዓመት ብድኑ የተቀላቀሉት የኢትዮጵያ እና ግብፅ መሪዎችም በስብሰባው ተድመዋል፡፡ ከስብሰባው ጎን ለጎን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ እና የግብፅ ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጣፋ መደቡሊ የሁለትዮሽ ስብሰባ ማድረጋቸው ተሰምተዋል፡፡
በውይይቱ ዋና ጉዳይ የአባይ ግድብን አፈፃተም እና የሕግ አቋም ላይ እንደነበር ምንጮች ጠቁመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ የግድቡ ሥራ ሙሉ በሙሉ እንደተጠናቀቀ ገልጸው፣ በአገሩ የተሻሻለ ኃይል ምርትና የአከባቢ አገራት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ እንደሆነ ማብራራታቸው ተሰምተዋል፡፡ ግድቡ ለግብፅ ወይም ለሱዳን አደገኛ እንደማይሆንም አረጋግጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር መድቡሊ ደግሞ የግብፅ ታሪካዊ እና ህጋዊ መብቶች በአባይ ውሃ ላይ መጠበቅ እንዳለበት ገልጸዋል። ግብፅ በኢትዮጵያ ወይም በሌላ አገር የልማት ስራዎች ላይ ጣልቃ እንደማትገባ በመግለጽ ነገር ግን የውሃ ሀብት መብቷን ማጣት እንደማትፈልግ ምገለፃቸው ተሰምተዋል፡፡
ጠቅላ ሚኒስትር አብይ አህመድ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ ክረምቱ ጋብ ሲል መስከረም ላይ እንደሚመረቅና ሱዳንና ግብጽምን በምርቃት ስነ ስርዓቱ እንዲታደሙ መግለጻቸው ተከትሎ ግብጽ ስትዝት እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡