
ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ አሜሪካ የሚያስፈልጋት ዘይት፣ ወርቅ፣ የብረት ማዕድን፣ ማንጋኒዝ እና የመሳሰሉት ነው ሲሉም መሪዎችን ተናግርዋቸዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ 5 የአፍሪካ መሪዎች ወደ ዋት ሃውስ መጋበዛቸው ይታወሳል፡፡ የተጋበዙበት ምክንያትም በንግድ ታሪፍ ጉዳይ ለመወያተ እንደሆነ ተገልፆ ነበር፡፡ ሆኖም ትራምፕ የሴኔጋል፣ ጊኒ ቢሳዋ፣ ሞውሪታኒያ፣ ላይበሪያ እና ጋቦን መሪዎች ትላንት ባስተናገዱበት ወቅት የመጀመሪያ ጥያቄያቸው ስለ መአድናት እንደነበር አልጀዚራ ዘግበዋል፡፡
ይህም አሜሪካ የአፍሪካ የተፈጥሮ ሃብት የመበዝበዝ ፍላጎት ያሳየ ነው እየተባለ ነው፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ዘመናዊ ቅኝ ግዛት ሲሉት ተደምጠዋል፡፡
ሌላው የአለም ሚድያዎች እያነጋገረ ያለው ጉዳይ ትራምፕ ለላይበሪያው ፕሬዝዳንት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ከየት እንደተማሩ መጠየቃቸው የሚመለከት ነው፡፡ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እሮብ እለት የአፍሪካ መሪዎችን ባስተናገዱበት ወቅት ብዙዎቹም የተለያየ ቋንቋ ከተናገሩ በኃላ፣ የላይቤሪያው ፕሬዝዳንት ጆሴፍ ባኮይ ማይክሮፎናቸውን ይዘው “ላይቤሪያ የአሜሪካ የረዥም ጊዜ ወዳጅ ናት እናም አሜሪካን እንደገና ታላቅ ለማድረግ በእርስዎ ፖሊሲ እናምናለን፤ ለዚህ እድል ብቻ ልናመሰግንህ እንፈልጋለን” እያሉ መናገር ሲቀጥሉ ትራምፕ በመሃል አቋርጦ “እንዲህ ያለ ጥሩ እንግሊዘኛ፤ እንዲህ በሚያምር ሁኔታ መናገር የት ተማርክ?” ብሎ ሲጠይቁዋቸው ይሰማሉ፡፡
ቦካይ እንደመሳቅ ሲሉ ትራምፕ “ላይቤሪያ ውስጥ?” ብሎ እንደገና ሲጠይቁዋቸው የወጣው ምስል ያሳያል፡፡ “አዎ ጌታዬ” ሲሉ ቦአካይ ሲመልሱ ትራምፕ አስከትሎ “ይህ በጣም አስደሳች ነው፤ በዚህ ጠረጴዛ ላይ እንዲዚህ መናገር የማይችሉ ሰዎች አሉኝ” በማለት በየቋንቋቸው ለተናገሩ መሪዎች በአሽሙር ሲወሩፈዋቸው ተሰምተዋል፡፡ ይህ ክስተት ትራምፕ ለአፍሪካዊያን ያላቸው የተሳሳተ አመለካከት ያሳየ ነው የሚሉት ብዙ ናቸው፡፡