ዲፕሎማሲ

10 ሀገራት የብሪክስ አጋር ሀገር ሆነው ተቀላቀሉ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች የተወጣጡ 10 ሀገራት ለብሪክስ እንደ አጋር ሀገር ሆነው መቀላቀላቸው ተገልፀዋል። ናይጀርያና ኡጋንዳ ከአፍሪካ ብሪክስን በአጋርነት ተቀላቀሉ ሃገራት ሆነዋል፡፡

ብሪክስን አጋር ሆነው የተቀላቀሉት ሀገራት ቤላሩስ፣ ቦሊቪያ፣ ካዛኪስታን፣ ኩባ፣ ናይጄሪያ፣ ማሌዢያ፣ ታይላንድ፣ ቪየትናም፣ ዩጋንዳ፣ ኡዝቤኪስታን ናቸው፡፡ አገራቱ መቀላቀላቸው የታወቀው በብራዚል እየተካሄደ ባለው የብሪክስ አባል አገራት ስብሰባ ነው፡፡

ባለፈው ዓመት ኢትዮጵያን ጨምሮ 6 አሀገሮች የብሪክስ አባል አገራት በመሆን መቀላቀላቸው ይታወሳል፡፡ ብራዚል፣ ሩስያ፣ ቻይና፣ ህንድና ደቡብ አፍሪካን በመያዝ እ.አ.አ በ2009 የተቋቋመው ብሪክስ ባለፈው ዓመት ግብጽ፣ ኢትዮጵያ፣ ኢንዶኒዥያ፣ ኢራን፣ ሳውዲ ዓረቢያና የተባበሩት ዓረብ ኢሚሬትስ በማካተት ኣባል አገራቱን ወደ 10 ከፍ ማድረጉ የሚታወስ ነው፡፡ አሁን ደግሞ በአጋርነት 10 አገራትን አካትተዋል፡፡

የእነዚህ አገራት መጠናከር የምዕራቡ ጎራን በኢኮኖሚ እና ወታደራዊ ዓቅምን የሚገዳደር ነው እየተባለ ነው፡፡

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates