መካከለኛ ምስራቅ

ሊባኖስ በእስራኤል ጦር ተመታች፡፡

ከጋዛ ወደ እስራኤል ሮኬት መወንጨፉ ተሰምቷል

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ እስራኤል በበርካታ የሊባኖስ አካባቢዎች ላይ ከባድ የአየር ጥቃት መሰንዘርዋ ተገልፀዋል፡፡

የእስራኤል አየር ሀይል  በመላ ሊባኖስ ጥቃት ማደረሱን ከቤይሩት የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ። ተዋጊ ጀቶቹ በቦዳኢ ከተማ በምስራቃዊ ሊባኖስ  ቢያንስ ሶስት ጥቃት ማድረሳቸው ተነግሯል። ተጨማሪ ሶስት ጥቃቶች በአርዚ እና ቡርጅ ራሃል ከተሞች በደቡባዊ ሊባኖስ መፈፀማቸው ተገልፀዋል፡፡ በሊታኒ ወንዝ እና በሌሎች በርካታ የደቡባዊ ሊባኖስ ክፍሎች ከባድ የአየር ጥቃት መፈጸሙን የቤይሩት ምንጮች አረጋግጠዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከጋዛ ወደ እስራኤል ሮኬት መወንጨፉ ተሰምቷል። የእስራኤል ጦር ሮኬቱ በኪቡትዝ አቅራቢያ መውደቁን ተረጋግጠዋል፡፡ የሃማስ ክንፍ  ቃሳም ብርጌድ በራጁም ሮኬቶች እስራኤል ላይ ጥቃት አድርሻለሁ ብሏል።

የእስራኤል እና የሃማስ  ድርድር በዶሃ ለጋዛ ስምምነት እና ታጋቾችን ለመልቀቅ እንደገና እንደሚጀመር እየተገለፀ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ዋይት ሀውስ ከመጎብኘታቸው በፊት ነው።

ኔታንያሁ ቀደም ሲል የጦርነቱ ቁልፍ አስታራቂ ወደሆነችው ኳታር ቡድን እየላኩ መሆኑን አስታውቀው ነበር፡፡ አርብ ዕለት ሃማስ በድርድሩ “ወዲያውኑ እና በቁም ነገር ለመሳተፍ” ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates