ኢትዮጵያፖለቲካ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ ፓርቲ በምርጫ 2018 ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀመጠ፡፡

ኢትዮ ሞኒተር፡ 30/1/2017፡ ኦፌኮ ከተመድ የውጭ መረጃ አሰባሳቢ ልዑክ ጋር በ2018 ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ የምርጫ ቦርድን እንደገና ማዋቀርን ጨምሮ ቁልፍ ጥያቄዎችን አቀረበዋል፡፡

የኦሮሞ ፌዴራላሲት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር በ2018 ዓ.ም. በሚካሄደው 7ኛው ዙር አጠቃላይ ምርጫ ዙርያ ውይይት ማድረጉን አስታውቀዋል።

በኦፌኮ ዋና ጽ/ቤት በተካሄደው ስብሰባ ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሱልጣን ቃሲም የተገኙ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ህብረት ቢሮ (UNOAU) የምርጫ ድጋፍ ክፍል ዋና ኦፊሰር የሆኑት አኪንየሚ ኦ. አዴግባላን ጨምሮ አራት አባላትን የያዘ ልዑክ መገኘቱን ከፓርቲው ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኦፌኮ በስብሰባው ላይ ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ተአማኒነት ያለው የምርጫ ሂደት እንዲረጋገጥ መንግስት ሊያሟላቸው የሚገቡ “መሰረታዊ” ጥያቄዎችን ማቅረቡ ተጠቁሟል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ኦፌኮ በ2018 ምርጫ ላይ መሳተፉ ሙሉ በሙሉ “በመሠረታዊ እና በተጨባጭ ለውጦች” ላይ የተመሰረተ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑን ማስረዳታቸውን ተገልፀዋል።

Show More

Related Articles

ምላሽ ይስጡ

ኢ-ፖስታ አድራሻወ ይፋ አይደረግም። መሞላት ያለባቸው መስኮች * ምልክት አላቸው

  (To Type in English, deselect the checkbox. Read more here)
Back to top button
Lingual Support by India Fascinates